Saturday, August 15, 2015

“ጓሃፍ ጽረጉለይ” (እነዚህን ቆሻሾች አስወግዱልኝ) አቶ መለስ ዜናዊ ያጠፏቸው የፓርቲው ሰዎች


በ1984 አ.ም አቶ መለስ ዜናዊ የተወሰኑ የፓርቲውን ቁልፍ ሰዎች ሰብስበው አጠር ያለች ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፉ ። እንዲህ ሲሉ “ጓሃፍ ጽረጉለይ” “እነዚህን ቆሻሾች አስወግዱልኝ” ነበር ያሉት ። በእርግጥም (“ቆሻሻ“)የሚለው ትርጉም አይገልጸውም ። ጓሃፍ ለማየት የምትጠየፈውን አስቀያሚ ቆሻሻ አይነት ሃሳብ ነበር የእርሳቸው ገለጻ ።
መለስ በዚህ ቃል ተጠቅመው
“አስወግዱልኝ” ያሉትን 36 ሺህ የህወሃት ታጋዮችን ነበር ።ትእዛዙም ተግባራዊ ተደረገ ። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ተበትነው ለጎዳና ህይወት ተጋለጡ ። ይህንን እርምጃ የተቃወሙ የበታች መኮንኖች እና የተወሰኑ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በ1986 አ.ም በሆለታና ታጠቅ እስር ቤቶች ተወረወሩ ።በተለይም በሆለታ እስር ቤት ውስጥ የተወረወሩት አምስት ሺህ መኮንኖች ሲጠቀሱ ፣በመለስ ዜናዊ የተለጠፈባቸው “ወንጀል ተብዬ” «መፈንቅለ ፓርቱ /በመንግስት ላይ ለማድረግ ሲያሴሩ» የሚል ነበር ።
ከአንድ አመት ለበለጠ ጊዜ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በአስከፊ እስር አሳለፉ። በሆለታ የእስር ካምፕ የሚበቅል እንዶድ የተባለ መርዛማ ቅጠል ሲኖር ፣ይህ ተክል በአካባቢው ህብረተሰብ ለልብስ ማጠቢያነት የሚያገለግል ነው ። አንድ ሺህ አምስት መቶ እስረኛ መኮንኖች ይህንን አደገኛ መርዛማ ቅጠል ጨቅጭቀው በማጠጣት በሞት አሸለቡ ። በትልቅ ጉድጓድ የሁሉም ሬሳ ተነባብሮ አፈር ለበሰ ። ከነዚህ ሟቾች መካከል አስራ አንዱ የክፍለጦር መሪዎች የነበሩ ሲሆን እነርሱም ኮ
/ል ጀብር፣ኮ/ል ኢሳያስ (ባጋ)፣ኮ/ል ወዲግትራ፣ኮ/ል ሽግረ ፣ኮ/ል ወልዳይ፣ኮ/ል ወዲ ቀጭን ፣ኮ/ል ወዲ ባርያ እና አብርሃም አሰፋ የተባሉት ይገኙበታል ። በተጨማሪም በሁለቱም እስርቤቶች ከ2ሺህ የሚበልጡ እስረኛ መኮንኖች በተላላፊ ሳንባ በሽታ ያለቁ ሲሆን ይህ መረጃ በፎቶግራፍ ጭምር ተደግፎ በኢትዮጵ ጋዜጣ በ1994አ.ም በተከታታይ ይፋ መደረጉን ለመጠቆም እወዳለሁ ።
በ1988 አ.ም ከሁርሶ ማሰልጠኛ ካምፕ ታፍነው የተወሰዱት ሻለቃ መኮንኖች ባዶ 6 በሚባል የግፍ እና የማሰቃያ እስርቤት ውስጥ ለ15 ቀናት በጨለማ እንዲታሰሩ በመደረጉ አይናቸው ታውሮ ተገኝቶአል ።ይህንን መረጃ ለጀነራል ሳሞራ የኑስ በወቅቱ የጠቆመው ሻለቃ ገ/እግዚአብሄር የተባለው መኮንን በዛው አመት ወደ ሩዋንዳ የዘመተውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአዛዥነት እየመራ በሄደ በማግስቱ «ወታደራዊ ተሽከርካሪ በስህተት ገጨው »ተብሎ ሬሳው ወደ አገር ቤት እንዲመጣ ተደረገ ። ነገር ግን ሆን ተብሎ በጥይት ነበር የተገደለው ። በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የሰራዊቱ አባሎችን በተለያየ የጥፋት ወጥመድ ያስወገደው የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ብዙም ሳይቆይ የተሻገረው ወደ ሰራዊቱ መሪ ጀ/ል ሃየሎም አርአያ ነበር ።መጀመሪያ ሰራዊቱን ማዳከም ያስፈለገው ይህንኑ ግድያ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሆን ሻእቢያና ህወሃት ባቀነባበሩት መሰረት የሃየሎም ግድያ ተከናውኗል።
ከ1984 አመተ ምህረት ጀምሮ ለ6አመታት የኢምግሬሽን መምሪያ ዋና ሃልፊ ሆነው ያገለገሉት አቶ ጸጉ በላይ በግፍ ተሰቃይተው ለህልፈት የበቁት በ1990 አ.ም. ሲሆን በእርሳቸው የተተካው የብአዴን አባል ግዛቸው ከአመት በሁዋላ እስርቤት ተወርውሮ ታሞ ተሰቃይቶ ሞተ ። በ1993 አ.ም. በመለስ ዜናዊ ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ ዘመቻ የጀመሩት ብ/ጄነራል በርሄ ገ/እግዚአብሄር « ባለቤቱ ገደለችው» በሚል የተቀናበረ የጥፋት ድራማ በቤላ ወታደራዊ ካምፕ ባልና ሚስቱ በሌሊት ተገድለው ተገኙ ። የህወሃት ማ/ኮሚቴ አባል ገ/መስቀል ሃይሉ እንዲሁም ቤተሰቡንም ጭምር በመረበሽ ለህልፈት እንዲበቃ ተደርጓል ። የደህንነቱ ሹም ክንፈ ገ/መድህን ግድያ በአባዱላ ስጋ ዘመድ በኮሎኔል ታምራት እንዲሁም በጀነራል ሳሞራ ተላላኪ ሻለቃ ነፋሂቶ የሴራ አቀናባሪት በሻለቃ ጸሃዬ ተፈጻሚ እንዲሆን ተደረገ ። ክንፈ ሲገደሉ አጠገቡ ጀነራል ሳሞራ እና ጀነራል ወዲ መድህን እንደነበሩ ለመጠቆም እሻለሁ ።
የአሁኑ የቴሌ ባለስልጣን አቶ ደብረጽዮን በወቅቱ በደህንነት ቢሮ የክንፈ ምክትል ሆነው አገልግለዋል ። ከክንፈ ግድያ ጋር በተያያዘ ሴራውን አውቀው የተቃውሞ አቋም በማራመዳቸው ወደ ትግራይ ተወስደው ለአራት አመታት በቁም እስረኛነት ከቆዩ በሁዋላ
“ተሃድሶን ተቀብያለሁ” ብለው ለመለስ በመናዘዛቸው አሁን ለሚገኙበት ስልጣን በቅተዋል ።ከክንፈ ግድያ ጋር በተያያዘ የደህንነት ም/ዳይሬክተር ነጋሲ ታፍኖ በቤተ መንግስት ምድር ቤት ውስጥ ለብዙ ቀናት ከተሰቃየ በሁዋላ ታጠቅ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተወስዶ በጥይት ተደብድቦ እንዲገደል እና አስከሬኑ አውሬ እንዲበላው ተደርጎአል። አስፋው የተባለ በደህንነት መምሪያ ሃላፊ ለ6 ወራት ታስሮ ከተለቀቀ በሁዋላ አእምሮው ተነክቶአል ።ከዚያም እርቃኑን ሆኖ በቦሌ ፍላሚንጎ አካባቢ ጎዳና ያድር የነበረው አስፋው ከ1995 ወዲህ በአካባቢው አልታየም። የደረሰበትም አይታወቅም ።
የቤተመንግስት የደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ዘርኡ መለስ ለብቻቸው ይኖሩበት በነበረው
«ኮከብ ሬስቱራንት (ሚልክ ሃውስ )» ህንጻ አንደኛ ፎቅ አንገታቸው በስለት ታርዶ ፣በድናቸው ተልቶ እና ተበላሽቶ የተገኘው በአምስተኛ ቀኑ ነበር ።
በተመሳሳይ በገርጂ የሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው በተቀመጡበት የሳሎን ወንበር በክራቫታቸው ታንቀው የተገደሉት የመገናኛ እና ትራንስፖርት ሚንስቴር ምኒስትር አቶ አየነው ቢተውልኝ ይገኙበታል። ባለስልጣናቱ የግፍ ጽዋ እንዲጎነጩ የተደረገው ከአቶ መለስ አመራር ጋር በፈጠሩት የሃሳብ
(አመለካከት)ልዩነት ብቻ እንደነበር ሊሰመርበት ይገባል። በሌላም በኩል የፓርቲው አባል የነበረው እና በስቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የ5ኛ አመት የህግ ትምህርት ሲከታተል የቆየው ጥላሁን መስፍን ሃምሌ 1996 አ.ም በበርካታ ጥይት የራስ ቅሉ ተቦዳድሶ ሞቶአል ።ግንቦት 1993 አ.ም. ኮሎኔል እሌኒ መለስ ለ11 ወራት በአንድ ክፍል ውስጥ ለብቻዋ ታስራ ተሰቃይታለች ።በዚያው ወቅት ወደ ታጠቅ ተወስደው ለ9 ወራት በእስር የተሰቃዩት የመከላከያ መረጃ ክፍል ሃላፊዎች ኮሎኔል ጎልያድ እና ኮሎኔል ኩህለን ሲጠቀሱ በታሰሩበት ወቅት ጎልያድ አእምሮው ተነክቶ ነበር

መለስ ያጠፏቸው የፓርቲው ሰዎች (እየሩሳሌም አርአያ)

No comments:

Post a Comment