ነኅሴ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ሱዳንዋ ዋና ከተማ ጁባ ማንነቱ ባልታወቀ ነፍጥ ባነገተ ታጣቂ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት አንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ሲገደል ሌሎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል። ማክሰኞ ዕረፋዱ ላይ በጁባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት ደጅ ላይ ዳቦ በመሸጥ ይተዳደሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎችን የገደለውና ያቆሰለው ግለሰብ እስካሁን አልተያዘም።
የአካባቢው ነዋሪዎች የሩምታ ተኩሱን ተከትሎ እንቅስቃሴያቸው የተገታ መሆኑንና ከቤት አለመውጣቸውን የአካባቢው የወጣቶች ተጠሪ ማጆር ዬን ለራዲዮ ታማዙጅ ገልፀዋል።
የጁባ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ዶክተር አብርሃም አደልት ፣ አንድ ሕጻንን ጨምሮ ሦስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሕክምና ማዕከሉ ከመጡ በሁዋላ አንዱ ህይወቱ ወዲያውኑ ማለፉን ገልጸዋል።ሌሎቹ ሁለት ቁስለኞች በሆስፒታሉ ውስጥ ተኝተው ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነው።በደቡብ ሱዳን ስርዓት አልበኝነትና ወንጀሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሱ መምጣታቸውን ራዲዮ ታማዙጅ አክሎ ዘግቧል።

No comments:
Post a Comment