Thursday, July 30, 2015

በረከት ስምኦን በህይወት መኖራቸውን ሳውዲ አረቢያ የተኙበት ሆስፒታል ሊያረጋግጥ አልቻለም – ጎልጉል

በረከት ስምኦን በህይወት መኖራቸውን ሳውዲ አረቢያ የተኙበት ሆስፒታል ሊያረጋግጥ አልቻለም – ጎልጉል
July 30, 2015 – Mereja.com — 10 Comments ↓
Bereket Simonጅዳ ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በድብቅ ገብተው የልብ በሽታ ህክምና የተደረገላቸው የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ሹም በህይወት መኖራቸውን እንደሚጠራጠሩ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ምስጢራዊ ምንጮች አረጋገጡ፡፡

በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ለህክምና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ህክምናቸውን ተከታትለው ወደ ሃገር ከተመለሱ ወዲህ የጤንነታቸው ሁኔታ እምብዛም ባለመስተካከሉ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ወደ ሳውዲ አረቢያ “ብግሻን” ሪፈራል ሆስፒታል ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡

አቶ በረከት ስሞኦን ከብስጭት፣ ከተለያዩ የአልኮል መጠጦችና ከአእምሮ አደንዛዥ እጽ እንዲርቁ ተመክረው ጤንነታቸው አስተማማኝ ደረጃ እስኪደርስ የሐኪሞች ቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ተነግሯቸው በቀጠሮ ቢሸኙም የቀጠሮ ግዜያቸውን አክብረው ዶክተሮቻቸው ጋር መቀረብ አለመቻላቸውን የሚገልጹ የሆስፒታሉ ምንጮች በረከት በህይወት መኖራቸውን ይጠራጠራሉ።

ጅዳ “ብግሻን” ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና የተደረገላቸው የኢህአዴጉ ሹም ጤንነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለውጥ አሳይቶ እንዳልነበር ሙያዊ ትንታኔ የሚሰጡ ምስጢራዊ የሆስፒታሉ ምንጮች በሽታው የልብ እንደ መሆኑ መጠን ባልታሰበ ግዜ ባለስልጣኑን ለሞት ሊዳርጋቸው እንደሚችል ከአቶ በረከት ጋር ለመጣ አስታማሚ ገልጸው እንደ ነበር ያስታውሳሉ።

በዚህም መስረት አቶ በረከት ስሞዖን ለሶስተኛ ግዜ ልባቸውን መታየት እንዳለባቸው ተነግሯቸው ቢሰናበቱም በቀጠሮ ቀን ተገኝተው ህክምናቸውን መከታተል ባለመቻላቸው በጤናቸው ላይ ሊያደርስ የሚችለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳየው የምርመራ ውጤት በረከት ሌላ ሃገር ለህክምና ሄደው ካልሆነ በቀር አሁን ባሉበት ሁኔታ የልብ በሽታው አደጋ ላይ ሊጥላቸው እንደሚችል በመጥቀስ ባለስልጣኑ በህይወት የሉም የሚለውን ጥርጣሬ ያጠናክራሉ።

በአቶ በረከት ስምዖን ጤንነት ዙሪያ ከጅዳ “ብግሻን” ሆስፒታል ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን። (goolgule.com)

Source: goolgule.com

No comments:

Post a Comment