Saturday, July 25, 2015

ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው:: – በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው


July 25, 2015 – ምኒሊክ ሳልሳዊ
ወያኔ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ ፓርቲዎችን በአዲስ አበባ ደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስብ ነው::-በወያኔ እና በአልሸባብ መካከል ተጋግሎ የቀጠለው ጦርነት የኦባማና ባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ ነው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)​-የወያኔው ጉጅሌ አገዛዝ የሻእቢያ ተቃዋሚ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማስታጠቅ እና በማደራጀት ዙሪያ በደሳለኝ ሆቴል ሊሰበስባቸው መሆኑ ተሰምቷል::በመጭው ሳምንት የሚሰበሰቡ እና በስብሰባው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪው የቀረበላቸው የኤርትራ የፖለቲካ ድርጅቶች:-

1 Eritrean People Congress,
2 Democratic Front for Eritrea Unity,
3 Eritrea Liberation Front,
4 Eritrea Democratic Party,
5 Eritrean Democratic Movement ,
6 Eritrean Nahda Party,
7 Eritrean Islamic Party for Development & Justice,
8 Red Sea Afar Democratic Organization,
9 Eritrean Islamic Congress”……….ናቸው:: እነዚህ ድርጅቶችን ወያኔ በራሱ ሰው ሃይል አዋቅሮ በማስታጠቅ እና በማደራጀት ፊት ለፊት አስቀድሞ የሻእቢያን መንግስት የመገርሰስ ሕልሙን የሚያሳካበት ስብሰባ መሆኑ ተጠቁሟል::ሻእቢያ በኤርትራ ምድር ላይ የወያኔን መንግስት ልመጣል የሚታገሉ ድርጅቶችን በማደራጀት እና በማስታጠቅ እየረዳ እንደሚገኝ ይታወቃል::ወያኔ እንዲሁ በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ ቀደም ሲረዳቸው የነበሩ ድርጅቶችን አሁን በመሳሪያ ለማስታጠቅ እንዳሰብ ታውቋል::ባለፈው ወር በጎንደር ተሰብስበው የነበሩ ድርጅቶች እርስ በርስ አለመግባባት እንደታየባቸው ሲነገር ሰንብቷል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ኢትዮጵያ የኦባማ መምጣት ከተሰማ በኋላ በወያኔ እና አልሸባብ ሰራዊቶች መካከል ጦርነቱ ታጋግሎ መቀጠሉ የኦባማ እና የባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ እና ሽብርን እየተዋጋን ነው በሚል የማጭበርበሪያ ስልት መሆኑ ታውቋል::በወያኔ ትንኮሳ የተነሳው ጦርነት እስካሁን ያልበረደ ሲሆን የውስጥ ጉዳዮችን እና ውጥረቶችን በመሸፋፈን ሽብርን እየተዋጋሁ ነው በሚል ሰበብ ከአሜሪካ ከፍተኛ ድጋፍን እና የገንዘብ እርዳታን ለማግኘት የሚደረግ መራወጥ መሆኑ ተጠቁሟል::ይህ የኦባማን እና የባለስልጣኖቻቸውን አትኩሮት ለመሳብ የተጀመረው ጦርነት ከኦባማ ጉብኝት በኋላ እንደሚቆም ምንጮቹ ገልጸዋል::ጦርነቱ ምንም የማይፈይድ እና ወታደሮችን ከመገበር ውጪ አዋጪ ያልሆነ የባለስልጣናት ኪስ በአሜሪካ ዶላሮች የሞሞላ መሆኑ ታዛቢዎች ይናገራሉ::#ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment