Monday, June 8, 2015

የኢህአዴግ ካድሬዎች ግብዣ ላይ እርስ በእርሳቸው ተደባደቡ


ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየካ ክፍለ ከተማ የግንቦት 16/2007 ዓ.ም የምርጫ ውጤት እንዲሁም የግንቦት 20 በዓልን ለማክበር ግንቦት 292007 ዓ.ም ባዘጋጀው ግብዣ ላይ የኢህአዴግ ካድሬዎች እርስ እርሳቸው መደባደባቸውን ምንጮች ገለጸዋል፡፡ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 መሰብሰቢያ አዳራሽ በተደረገው ግብዣ ብዙ ወጭ የፈሰሰበትና በርካታ የኢህአዴግ ካድሬዎች የተገኙበት እንደነበር የገለፁት ምንጮቹ፣ ስጋና ሌሎች ለግብዣው የቀረቡ ምግቦች
ተሰርቀዋል በሚል እርስ በእርስ መደባደባቸው ታውቋል፡፡
ከስጋና ከሌሎች የምግብ ቁሳቁሶች ከወጣው ወጪ ሰርቀዋል በሚል ሰበብ ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው መካከል የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የኢህአዴግ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ በላይነህ ሙሉነህ ይገኙበታል፡፡ አቶ በላይነህ
በግጭቱ ወቅት በመጎዳታቸው በአሁኑ ወቅት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኙም ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡ አቶ ሙሉነህ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል የኦህዴድ አባል ናቸው።

No comments:

Post a Comment