Thursday, May 28, 2015

የኮሚኩ ምርጫ ወግ እንደለጠቀ ነው

ደብረ ብርሀን ነው፣ ኢህአዴግን በመወከል ለፓርላማው ይወዳደራል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ግለሰብ በህመም ሳቢያ ህይወቱ ያልፋል፡፡ እናም በእርሱ ምትክ ሌላ ተወዳዳሪ ይቀርብና ድምጽ የመስጠት ስነ ስርዓት መከናወን ይጀምራል፡፡ድምጽ በሚሰጥበት ዕለት በካድሬ ግፊት ከለቅሶ የተነሳችው የቀድሞው ተጠባቂ ዕጩ ባለቤት ሁለት የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ከአስመራጮች ይበረከትላታል፡፡
‹‹እኔ ብቻዬን ነኝ መስጠት የምችለውም አንድ ድምጽ ሆኖ ሳለ ለምን ሁለት የድምጽ ወረቀቶች ሰጣችሁኝ››በማለት በአግራሞት ትጠይቃለች፡፡
አስመራጩ ‹‹ባለቤትሽ በህይወት ቢኖር ኖሮ ይመርጥ ነበር፡፡ደግሞም ማንን ይመርጥ እንደነበር ስለምናውቅ ለመታሰቢያ እንዲሆነው ነው››ብለዋት አረፉት፡፡

No comments:

Post a Comment