ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመታ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ከሰኞ
ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር መጋጨታቸው ታውቋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ነዋሪዎቹ በምርጫው ማግስት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲጀመሩ በጸጥታ ሃይሎች የተከለከሉ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ አርብቶአደሩ በወሰደው እርምጃ 3 ፖሊሶች ቆስለዋል። በአካባቢው በአርብቶ አደሩና
በወረዳው ፖሊስ መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በአሁኑ ጊዜ አካባቢው በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት ተከቧል። ሆቴል ቤቶችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመዘጋጀታቸው ህዝቡ ለከፍተኛ
ችግር መዳረጉንም ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮምያ በቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ” የምርጫ ካርድ አልቋል በሚል በእለቱ ሳይመርጡ የቀሩ ተማሪዎች ዛሬ እንዲመርጡ ተደርጓል። ባለፈው እሁድ ተማሪዎች ተቃውሞ በማስነሳታቸው በርካታ ተማሪዎች
መደብደባቸውና መቁሰላቸው መዘገቡ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ በርካታ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው ወጥተው በቤተክርስቲያኖችና በግለሰቦች ቤት ያለፉትን ሁለት ቀናት አሳልፈዋል። ተማሪዎች የታሰሩ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱ ፣ ካልተፈቱ
ትምህርት እንደማይጀምሩ ሲያስታውቁ ቆይተዋል። ዛሬ ተማሪዎች ድምጽ እንዲሰጡ ሲደረግ፣ የተወሰኑ ተማሪዎች ተገኝተው ድምጽ ቢሰጡም አብዛኛው ተማሪ ምርጫው ማለቁ ከተነገረ በሁዋላ አንመርጥም ብለዋል።
በአካበባው ስላለው ሁኔታ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የሰማያዊ ፓርቲ ተወዳዳሪ አቶ ጌታቸው በቀለ በቦረና ዞን ምርጫው የይስሙላና የውሸት ፣ አይን ያወጣ አረፋ የታየበት ነበር ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል
ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግ መቶ በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን መውሰዱን ገልጿል። በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ከ23 መቀመጫዎች 23ቱን፣ በትግራይ ከ31 መቀመጫዎች 31፣ በአማራ ከ107 ወንበሮች 107ቱ፣ በኦሮምያ
ከ150 ወንበሮች 150 እንዲሁም በደቡብ ክልል ከ95 መቀመጫዎች 95ቱን አግኝቷል። ከአጋር ድርጅቶቹ መካከል በሶማሊ ክልል ሶህዴፓ 16 ወንበሮችን፣ በ ቤንሻንጉልጉሙዝ ቤጉዴፓ 7፣ በድሬዳዋ ኢህአዴግና ሶህዴፓ እንዲሁም
በአፋር አብዴፓ 6ቱን ወንበሮች ተከፋፍለዋል።
ኢህአዴግ ትንሽ ወንበር ለተቃዋሚዎች በመልቀቅ ምርጫውን ተአማኒ ለማስደረግ የምክራል ቢባልም፣ ወንበሮችን ሙሉ በሙሉ ጠቅልሎ ወስዷቸዋል። ኢህአዴግ 100 በመቶ ምርጫ በማሸነፍ የአፍሪካን የምርጫ ሪከርድ መስበሩ እየተነገረ
ነው።
አርበኞች ግንቦት7 ዛሬ ባወጣው ርዕሰ አንቀጽ የዘንድሮው ምርጫ 2007 ከዚህ በፊት ከነበሩ በባሰ ለአፈና የተጋለጠ የነበረ መሆኑ ከጅምሩ በግልጽ መታየቱን ገልጿል።
ህወሓት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የምርጫ ጉዳይ እና የምርጫ ፓለቲካ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም መጠናቀቁን የሚያስታውሰው አርበኞች ግንቦት7፣ ህወሓት ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ የሚወርደው ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽን
ባቀናጀ ሁሉገብ ትግል ነው ብሎአል።
ንቅናቄው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ወይም በህቡዕ በመደረግ ትግል ተቃውሞውን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባለውና አቅሙ በሚመቸው የትግል ዘርፍ ይሳተፍ ያለው ንቅናቄው፣ ሕዝባዊ
ኃይልን መቀላቀል የቻለ ይቀላቀል፤ ያልቻለው በያለበት ተደራጅቶ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግሉን ይቀጥል ብሎአል።
“እያንዳንዳችን ከሚመስሉንና ከምናምናቸው ጋር ተነጋግረን አገዛዙ የሸረሸረብንን በራስ መተማመን እና የእርስ በርስ መተማመንን መልሶ በመገንባት ውስጥ ውስጡን ጠንካራ አገራዊ ኅብረት መፍጠር “እንደሚያስፈልግ የገለጸው ንቅናቄው፣
እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ታጥቆ እንዲነሳ፤ ወደ ተግባራዊ ትግል ፊቱን እንዲያዞር ጥሪ አቅርቧል።

Source:http://ethsat.
No comments:
Post a Comment