Friday, May 29, 2015

ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው የአንድ ሳምንት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባት፡፡


ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ ችሎት የቀረበችው ወ/ሮ ንግስት፣ መንግስት በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ በአይ.ኤስ.አይ.ኤስ የሽብር ቡድን የተፈጸመውን
የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና ሰላማዊ ሰልፍን በማወክ›› ተጠርጥራ እንደታሰረች ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ፍርድ ቤት በምን ወንጀል ተጠርጥራ እንደታሰረች ወ/ሮ ንግስትን በጠየቃት ጊዜ ‹‹በምን እንደታሰርኩ አላውቅም፤ ቤቴ ድረስ መጥተው ከልጄ ጋር እስር ቤት አስገብተውኛል›› ስትል መልሳለች፡፡ ፖሊስ በወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ላይ
የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የአንድ ሳምንት ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለታል፡፡
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ስለጠየቀው የጊዜ ቀጠሮም ሆነ ስለ ዋስትና ጉዳይ የወ/ሮ ንግስትን ሀሳብ ለማዳመጥ አለመቻሉንም ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ንግስት ለመናገር ፍርድ ቤቱን በጠየቀች ጊዜ እድሉ ተነፍጓታል።

No comments:

Post a Comment