Tuesday, May 5, 2015

ምርጫ 2007 ምርጫ ሳይሆን ከፍተኛ ገንዘብ ማስገኛና የምዝበራ ቢዝነስ - ሚሊዮኖች ድምጽ








ለምርጫዉ ቅስቀስ ምርጫ ቦርድ ከመደበው ገንዘብ 15 ሚሊዮን ብር የሚሆን ለኢሕአዴግ ሲሰጥ፣ ለ 270 መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎችን ላሰለፈው መድረክ፣ 2 ሚሊዮን ብር፣ ለ165 እና ለ139 መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎች ላሰለፉት ኢዴፓና ሰማያዊ ወደ ስምንት መቶ ሺህ ብር የተመደበላቸው ተመድቦላቸዋል። ለትግስቱ አወሉ ቡድን ግማሽ ሚሊዮን ብር ተፈቅዶለታል።

አንድ የፓርላማ ተወዳዳሪ ብቻ ያሰለፉ ድርጅቶች ወደ አምሳ ሶስት ሺህ ብር ድጋፍ ከምርጫ ቦርድ አግኝተዋል ። ለምሳሌ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ እና የሶዶ ጎርዳና ህዝቦች ፓርት እያንዳንዳቸው አንድ የፓርላማ ተወዳዳሪ ብቻ ያሰለፉ ሲሆን ፣ እያንዳንዳቸው 53 790 ብር ተችረዋል። የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ 2 ተወዳዳሪዎች ብቻ ሲያሰለፍ፣ ወደ 55875 ብር ተለግሰዋል።

የምርጫው ሂደት በርግጥ ትልቅ ዘረፋ የሚደረግበት፣ ፓርቲ በማቋቋም ጥቅም የሚገኝበት ቢዝነስ እንደሆነ፣ የምርጫ ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ ቀመር በገሃድ ያመላከተበት ሁኔታ ነው።
ከአራባ ሰባት ለምርጫ ተወዳዳሪዎች ካሰለፉ ፓርቲዎች መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት ስ9 ድርጅቶች ከ20 በታች ተወዳዳሪዎችን ነው ለፓርላም ያሰለፉት። ሃያ ሰባት ድርጅቶች ( 57% ) ከአሥር በታች፣ ሃያ ድርጅቶች ደግሞ (42% ) ከአምስት በታች ነው ለፓርላማ ተወዳዳሪዎች ያሰለፉት። ይሄም ብዙ ፓርቲዎች አሉ የሚባለው ከገዢው ፓርቲ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳና መከርከሮያ ምን ያህል ባዶና እንደሆነ የሚያሳይ ነው።








No comments:

Post a Comment