መጋቢት ፩(ሚያዝያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችንን ሰሞኑን ለአማራ ክልል የሚሰጠውን የዘይት ክፍፍል መሰረት አድርጎ በላከው ዘገባ ለ20 ሚሊዮን ህዝብ በወር የተመደበው ዘይት 4 ሚሊዮን 800 ሺ ሊትር ነው። ለክልሎች የሚከፋፈለው ዘይት በህዝብ ቁጥር ልክ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት አጠቃላይ ስሌቱ ለአንድ ሰው በወር ሩብ ሊትር ዘይት መሆኑን ጠቅሷል። የክፍፍሉ መጠን ዘይት ባለበት ጊዜ የተሰላ ሲሆን፣ የዘይት አቅርቦት በማይኖርበት ጊዜ ከዚህ እንደሚያንስ ገልጿል። አብዛኛው የዘይት አቅርቦት አንድ ለአምስት ለሚደራጁ ሰዎች የሚሰጥ መሆኑም ፍትሃዊነቱ ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ገልጿል። መንግስት መሰረታዊ የሚባሉትን የፍጆታ እቃዎች ለሟሟላት እየተሳነው መምጣቱ፣ በየአመቱ አገኘሁ ከሚላው እድገት ጋር አብሮ ሊጣጣም አልቻለም።
Source: ethsat.com
No comments:
Post a Comment