Saturday, March 28, 2015

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች * ከዴሲሶን ሬዲዮ ያዳምጡ

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች * ከዴሲሶን ሬዲዮ ያዳምጡ

Deseon

የጦማርያንና ጋዜጠኞቹ አቤቱታዎች ውድቅ ተደረጉ

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሦስቱ ተወዳጅ ጋዜጠኞች መጋቢት 15/2007 ዓ.ም  የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡
 ተከሳሾች ባቀረቧቸው ሁለት አቤቱታዎች ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቶ የነበረ ሲሆን፡ በዚህም አንደኛ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ካለው ማስረጃ ዝርዝር ውስጥ 12 የኦዲዮ-ቪዲዮ ሲዲዎች አያይዞ ያቀረበ ቢሆንም፣ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች እስካሁን ባለመድረሳቸው ተከሳሾች የቀረበባቸውን ማስረጃ ተመልክተው መልስ ለማዘጋጀት ሲዲዎቹ እንዲሰጧቸው ያቀረቡት አቤቱታ ሲሆን፣ ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ 4ኛ ተከሳሽ ማህሌት ፋንታሁን እና 9ኛ ተከሳሽ ኤዶም ካሳዬ በቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ ከጎብኝዎቻቸው መከልከል ጋር በተያያዘ አቅርበውት በነበረው አቤቱታ ላይ ብይን መስጠት ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም ሁለቱንም አቤቱታዎች ውድቅ አድርጓል፡፡
የሲዲ ማስረጃውን በተመለከተ አቃቤ ህግ ማስረጃዎችን ኢግዚቪት ብሎ ስላስመዘገበ አሁን በዚህ ደረጃ ሲዲዎቹ ለተከሳሾች የሚደርሱበት አግባብ የለም በሚል ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን አቤቱታ እንዳልተቀበለው ገልጹዋል፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ማስረጃ በመስማት ሂደት ወቅት ማስረጃዎችን እየተመለከቱ መልስ እንዲሰጡ እንጂ ቀድሞ እጃቸው የሚደርስበት አሰራር የለም ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡
ፍርድ ቤቱ የቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር ላይ በሁለቱ ሴት ተከሳሾች የቀረበውን አቤቱታም ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ በተከሳሾች የቀረበውን አቤቱታ እና የእስር ቤቱ አስተዳደር የሰጠውን መልስ መመልከቱን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፣ ‹‹ለቀረበው አቤቱታ ማስረጃ ተያይዞ ያልቀረበ በመሆኑ…›› በሚል አቤቱታውን ውድቅ አድርጓል፡፡ ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ከሰኞ መጋቢት 21/2007 ጀምሮ ለሦሰት ቀናት ይሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡……..

ድምፃችን ይሰማ 2ኛውን የሰላማዊ ተቃውሞ ይፋ አደረገ

ከ መጋቢት 18/2007 ጀምሮ ሳንቲም በመሰብሰብና በማጠራቀም ራስ ላይ የመቆጠብ እቀባ በማድረግ ለመንግስት የተቃውሞ መልእክት ወደማስተላለፍ እንቅስቃሴ እንገባለን ያሉት ድም ችን ይሰማ ፡፡መንግስት በገዛ ህዝቦቹ ላይ በሃይማኖታችን ምክንያት እያደረሰብን የሚገኘው ከፍተኛ በደል  ከእኛው በሚሰበሰብ ግብር መሆኑ ግልጽ ነው ያሉ ሲሆን፡፡ ህዝቡን እየደበደቡ እና እየገደሉ ያሉት የመንግስት ኃይሎች ደሞዛቸው የሚከፈለውም ከህዝቡ ኪስ በሚወጣ ገንዘብ ነው፡፡ በመሆኑም እንደዜጋ ገንዘባችንን በራሳችን ላይ ኢንቨስት ያለማድረግ የዜግነት መብታችንን በመጠቀም የሳንቲም ዝውውሩ ላይ እጥረት ስንፈጥር በእርግጥም ከእኛ ኪስ የሚገኘው ገንዘብ ላይ እኛም እንደህዝብ የተወሰነ ስልጣን እንዳለን ለመንግስት ግልጽ እናደርጋለን። ጥያቄዎቻችንን ባለመመለሱም የተቃውሞ መልእክታችንን እናስተላልፋለን ብለዋል አክለውም
እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሃይማኖታችን ምክንያት በመንግስት ከፍተኛ በደል እየደረሰብን ያለን ሰላማዊ ዜጎች ብንሆንም መንግስት ከበደሉ ሊቆጠብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለዓመታት ሰላማዊ ትግል ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ሰላማዊነታችንን ለመግለጽ ነጭ ጨርቅ እያውለበለብን በአደባባይ በተገኘን ቁጥር መንግስት አስፈራርቶናል፤  ደብድቦናል፤ ዘርፎናል፤ አስሮናል፤ ገድሎናል፡፡ እኛ ነጭ ሶፍት ይዘን ሰላማዊነታችንን በአደባባይ ስንዘምር መንግስት ደግሞ ዝናሩን ታጥቆ በጥይት እሩምታ ተቀብሎናል፡፡ የማይጠፋ ጠባሳ የጣለ ጥቁር ሽብር ፈጽሞብናል፤ ፈርመን የላክናቸውን ወኪሎቻችንን በግፍ እስር እና በከፍተኛ ቶርቸር አሰቃይቶብናል፡፡ እስካሁንም ነጻነታቸውን ነፍጎ የምርጫ ቅስቀሳ መጠቀሚያ እያደረጋቸው ይገኛል። ስለዚህ አሁን ላይ መንግስት ጥይት ሊተኩስበት በማይችለው ሜዳ ሰላማዊ ተቃውሟችንን ከመቀጠል ውጭ ሌላ ምርጫ ያለን አይመስልም፡በማለት 2ኛውን የሰላማዊ ተቃውሞ ይፋ አድርገዋል
ይፋ ያደረጉት  የትብብር መንፈግ ተቃውሞ ዋነኛ ዓላማም እንደገለፁት መንግስት ጥይት የሚተኩስበት ዒላማ የማያገኝበትን የትግል ድባብ በመፍጠር መብታችንን የማጎናጸፍ ግዴታውን እንዲወጣ የተቃውሞ መልእክት ማስተላለፍ ነው፡፡ ብለዋል ወደፊትም አንድ ብርና ከዛም በላይ ያሉ የብር ኖቶችንም ከመሰብሰብ ጀምሮ ሌሎች በአተገባበራቸውም ሆነ በእንድምታቸው ጠንክረው እያደጉ የሚሄዱ የትብብር መንፈግ እና የቦይኮት ስልቶችን ቀስ በቀስ በመለማመድ ሰላማዊ ትግላችንን እስከድል ደጃፎች እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ ተመለሰ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹አናስተላልፍም›› ብለው መመለሳቸውን ድርጅቶቹ ለፓርቲው በላኳቸው ደብዳቤዎች ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የብሔራዊ ራዲዮ በአማርኛ ስርጭት የሚተላለፍ ‹‹መንግስታዊ አወቃቀር›› የሚል የቅስቀሳ መልዕክት ልኮ የነበር ሲሆን ባለፉት 24 አመታት ተግባራዊ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ለግጭት መንስኤ መሆኑን በመረጃ ዘርዝሮ ማቅረቡን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ  የገለፁ ሲሆን፡፡
ይሁንና ኢብኮ ይህን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹በተለያዩ ጊዜያት በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች በመዘርዘር በህዝቦች መካከል ሌላ ግጭት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ የሚያደርጉና ግጭት የሚያራግቡ፣ አንዱን ብሔር ከሌላ ብሔር የሚያገጩ ናቸው፡፡›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመልዕክቶቹ ውስጥ ‹የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት›፣ እንዲሁም ‹የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት› የሚለው አገላለጽ የፓርቲውን ህጋዊ መጠሪያ የማይወክል በመሆኑ›› በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡ ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል እነዚህ ግጭቶች በአሁኑ ወቅትም የቀጠሉና የጎሳ ፌደራሊዝሙ እስካለ ድረስ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን የገለጸው የፓርቲውየህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ መልዕክቶቹ ከፓርቲው ማንፌስቶ የወጡ፣ ኢብኮ እንዳለው ለግጭት ሳይሆን ከግጭቶቹ መማር እንዲቻልና አሁን ያለው የጎሳ ፌደራሊዝም ከተስተካከለ ችግሮቹ እልባት እንደሚያገኙ በሚያሳይ መልኩ የተላለፈ መልዕክት ነው ብሎአል፡፡ ‹‹እኛ ያቀረብነው አማራጫችን ነው፡፡ አማራጫችን ስናቀርብ ደግሞ የጎሳ ፌደራሊዝም የፈጠረውም ቀውስም በማሳያነት ማቅረብ አለብን፡፡ ይህን እውነታ የአገር ውስጥና የውጭ ተቋማት ዘግበውታል፡፡ አብዛኛዎቹ መንግስትም ያመነባቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን ስርዓቱ የሰራቸው ጥፋቶች ይፋ አውጥተን እንዳናቀርብ ስለተፈለገ መልዕክቱን መልሰውታል፡፡ በግልጽ አማራጫችን እንዳናቀርብ ተከልክለናል›› ሲል  ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ ዜና የአዲስ አበባ አስተዳደር መገናኛ ኤጀንሲ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት ‹‹ከሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ጋር የሚጻረር፣ ብሔር ብሄረሰቦችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት እንዲያመሩ የሚገፋፋ፣ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን ስም የሚያጎድፍ ይዘት የተካተተባቸው›› ናቸው በሚል መልሷል፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ሲመለስ ለ8ኛ ጊዜ መሆኑ ታውቃል፡፡
በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ባለስልጣን ላይ ህዝባዊ እርምጃ ተወሰደ!!
ከሳምንት በፊት ጎንደር ከተማ አንድ የወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ባለስልጣን በነጻነት ታጋዮች መገደሉን ተከትሎ በሰሜናዊ ያገሪታ ክፍል ዉጥረት የነገሰ ሲሆን ይኸዉ ብሶት የወለደዉ ጸረ ወያኔ እርምጃ ወደ መሀል ያገራችን ክፍል ተዛምቶ  ባሳለፍነው ሳምንት ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በኦሮሚያ ክልል አምቦ አከባቢ አንድ ከፍተኛ የወያኔ ወታደራዊ ባለስልጣን መገደሉ ታወቀ፥፥ በዚህም ምክንያት አምቦ በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር ስር የወደቀች ሲሆን፥፥ በቀበሌ 2 በተባለ አከባቢ ሲያልፍ የነበረውን የወያኔ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን የገደለው ማንነቱ ያልታወቀ ሲሆን አምቦ በከፍተኛ የደህንነት ቁጥጥር ስር ነች ያሉት ነዋሪዎቹ በጊዜው ጉዳዩን ያልተረዱና ከፍተኛ መደናገጥ እንደደረሰባቸው የተናገሩ ሲሆን ፖሊሶች እና ማንነታቸው የማይታወቁ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን እያስቆሙ እና እየፈተሹ እንደነበር ታውቋል፥፥ተመሳሳይ ጸረ ወያኔ እርምጃዎች በስርዓቱ ተላላኪዎችና የህዝብ እምባ አፍሳሶች ላይ በሀገሪቱ አራት ማዕዘን ተጠናክሮም መቀጠሉን ለማወቅ ተችላል።
ሩሲያን ከእንግሊዝ የሚያገናኝ እና 20 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚረዝም የፍጥነት መንገድን ለመገንባት ሃሳብ ቀረበ።
የምድራችንን ግማሽ ርቀት የሚሸፍነው እና የመተግበሩ ጉዳይ አጠያያቂ ነው የተባለው ይህ ፕሮጀክት  ከምዕራብ ሩሲያ በመነሳት ምስራቃዊ እንግሊዝን ጨምሮ አላስካ ድረስ የሚዘልቅ ነው።
የፍጥነት መንገዱ ከተገነባ አውሮፓን ከእስያ እና አሜሪካ በማገናኘት በትልቅነቱ የአለማችን የመጀመሪያው የፍጥነት መንገድ የሚሰኝ ይሆናል።
የሩሲያ የሳይንስ አካዳሚ ሃላፊ ቭላድሚር ፎርቶቭ “ትራንስ ዩሬዥያ ቤልት ዲቬሎፐመንት” የተሰኘውን እና በቅርቡ የመንገድ ግንባታውን እውን የሚያደርግ የፕሮጀክት ሃሳብ ለፕሬዚዳነት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል ነው የተባለው።
ሜይል ኦንላይን ዘ ሰርቢያን ታይምስን ጠቅሶ እንደዘገበው ሃላፊው ይህ ፕሮጀክት ጉጉት አዘል እና እጅግ ውድ  ቢሆንም በርካታ አህጉራትን በማገናኘት ብዙ ችግሮችን እንደሚፈታ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
እስካሁን የምድራችን ትልቁ የደረቅ ምድር የፍጥነት መንገድ 14 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው እና የአውስትራሊያ ግዛቶችን እርስ በእርስ የሚያገኛኘው የፍጥነት መንገድ ነው።
በፈንሳይ አልፕስ ተራራ ላይ ተከስክሶ የ150 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አደጋ፤ በረዳት አብራሪው አማካኝነት የተፈፀመ አንደሆነ የፈረንሳይ ባለስልጣናት አስታወቁ
ከስፔን ወደ ጀርመን ሲበር የነበረውና በፈንሳይ አልፕስ ተራራ ላይ ተከስክሶ የ150 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አደጋ፤ የአጋጣሚ አደጋ ሳይሆን ሆን ተብሎ በረዳት አብራሪው አማካኝነት የተፈፀመ አንደሆነ የፈረንሳይ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ባለስልጣኑ አንዳሉት አውሮፕላኑ ውስጥ ከምትገጠመዋ ጥቁር ሳጥን (black box) ላይ የተገኙ የድምፅ መቅጃዎች ላይ ዋና አብራሪው ረዳት እብራሪውን ሁሉን ነገር ተቆጣጠር ብሎት ከማብረሪያ ክፍሉ ውስጥ ሲወጣና በሩ ሲቆለፍ ድምፅ መሰማቱን ተናግረዋል። ከዛም አውሮፕላቱ በፍጥነት ወደመሬት መወርወር ጀመረ። ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የ28 ዓመቱ ወጣት ረዳት አብራሪ ለምን እንደዚህ እንዳደረገ ምንም የታወቀ ነገር የለም።

sou

No comments:

Post a Comment