Thursday, August 11, 2016

#‎OromoProtests‬ in the last hearing we filed a complaint why the Federal court is seeing our case but no response- Bekele Gerba


በጸረ ሽብር ህጉ ተከሶ፣በዛሬዉ ዕለት የዕምነት ቃላቸዉን እንዲሰጡ የተቀጠሩት እነ ጉርሜሳ አያኔ በሀገሪቱ የህግ የበላይነት ብሎ ነገር እንደሌለና የኢትዮጵያን ፍርድ ቤት የወያኔ የገደል ማሚቶ መሆናቸዉን በሚያረጋግጥ መልኩ ቃላቸዉን ሳይሰጡ ከፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ወጥቷል፡፡
ሁሉንም የተከሾች ክርክር በዚህ ገጽ ማቅረብ እጅግ አዳጋች ስለሆነ፡፡ጥቂቶቹን ብቻ ለማካፈል ተገደናል፡፡
ጥፋቱን ፈፅመዋል ወይስ አልፈጸሙም? ተብለዉ መጀመሪያ በመሃል ዳኛ የተጠየቁት ‘’ኦቦ ጉርሜሳ አያኖ’’ ነበሩ፣ኦቦ ጉርሜሳም ሲመልሱ ‘’ክሱ ግልፅ አልሆነልኝም እኔ ፖለቲከኛ ስሆን የመድረክ ፓርቲ-አባል ነኝ፡፡የእኛ ፓርቲ ህገመንግስቱን ተከትሎ የተቋቋመ ህጋዊ ፓርቲ ነዉ፡፡የተከሰስኩት ግን የኦነግ አባል ነህ በሚል ነዉ፣እኔ እስከማዉቀዉ አንድ ሰዉ የሁለት ድርጅት አባል መሆን አይችልም፡፡ይሄ ክስ መንግስት መሬቴን አሳልፌ አልሰጥም ያለዉን የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ አሸባሪ ብሎ እየከሰሰ ነዉ ያለዉ ስለዚህ ቃሌን ለዚህ ፍ/ቤት አልሰጥም’’፡፡ቀጠለ ኦቦ ደጀኔ ጣፋ ‘’የኢትዮጵያ ፍ/ቤት በግልፅ ህገመንግስቱን እያፈረሰ ያለ ተቋም ስለሆነ ለዚህ ፍ/ቤት ቃሌን አልሰጥም፣ከአሁን ወዲህም ወደዚህ ፍ/ቤት መምጣት አልፈልግም፣ዉሳኔዉም ግልጽ ስለሆነ ባለሁበት ሆኜ ይድረሰኝ!የኢትዮያ ህዝብ ግን እኛ ላይ የተፈጠመዉን በደል እንዲያዉቅልን እፈልጋለሁ’’፡፡
‘’አዲሱ ቡላላም’’ በተራዉ ‹‹የደረሰኝ ክስ የሚመስል ድርሰት ግራ አጋብቶኛል፡፡እኔ የመድረክ ፓርቲ እንጂ የኦነግ አባል አይደለሁም፣ለህዝቤ ብዬ በአደረግኩት ነገር በሙሉ ደስተኛ ነኝ፣በእ በአዲሱ ስም የተመሰረተዉ ክስ በኦሮሞ ላይ የተመሰረተ ክስ መሆኑን መሆኑን ሁሉም ሰዉ እንዲያዉቅልኝ እፈልጋለሁ፤ እኔ ለዚህ ፍትህ አልባ ፍ/ቤት ቃሌን መስጠት አልፈልግም ተመካክራችሁ ዉሳኔዉን ባለሁበት አድርሱኝ››!
‘’በቀለ ገርባ’’ ሲናገር ‹‹ባለፈዉ ቀጠሮ የክስ መቃወሚያችን ላይ ወንጀሉ ተፈጸመ የተባለዉ ኦሮሚያ ክልል ሆኖ ሳለ ለምን በፌዴራል መንግስት እንዳኛለን?! በክልላችን በቋንቋችን እንዳኝ ብለን አቤቱታ አቅርበን ነበር ቢሆንም የሰማን የለም፡፡እኛን ግን ገብቶናል ለምን ክሳችን በፌዴራል እንዲታይ እንደተደረገ፣ፍ/ቤቱ በተጻፈለት መሰረት ሊፈርድብን ነዉ፡፡ይሄ ፍ/ቤት ታዞ እንደሚሰራ ከዚህን በፊት ስምንት አመት ያለጥፋቴ ተፈርዶብኝ እኔ በራሴ ህይዎት ችግሩ ደርሶብኝ አይቻለሁ ስለዚህ ለዚህ ፍ/ቤት ቃሌን አልሰጥም››
ቀጠሉ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ እሳት የላሱ የእዉነት አምደኞች፡፡አንዱ ‹‹ጨለማ ዉስጥ ሆኜ ምንም ማዉረት አልፈልግም››
ሌላዉ ‹‹የህግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት ሀገር ላይ ሆኜ ለባስልጣናት ለሚታዘዝ ፍ/ቤት ቃሌን አልሰጥም››፡፡አንዱም እንዲሁ ተጠራና ተነሳ ‹‹እኛ ላይ የታወጀዉ የዘርማጥፋት ወንጀል ነዉ ስለዚህ ለዚህ ፍ/ቤት ቃሌን መስጠት አልችልም››
፣ሌላዉም ቀጠለ ‹‹የተከሰስኩት ኦሮሞ በመሆኔ ብቻ ነዉ››፡፡አሁንም ሌላኛዉ ሲጠየቅ አለ ‹‹የዘረኝነት በሽታ ያለባቸዉ ሰዎች ናቸዉ ያለትፋቴ የከሰሱኝ ቃሌን አልሰጥም››!ፍ/ቤቱ በዚህና በመሰል ከበባድ የእዉነት ቃሎች ልክ-ልኩ ተነግሮት ችሎቱ ተጠናቀቀ!



No comments:

Post a Comment