Monday, May 30, 2016

University Entrance Exam Cancelled after it was leaked

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሃሙስ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና እስካሁን ኮድ 12 የእንግሊዝኛ ፈተና መውጣቱ በመረጋገጡ ነው እንዲቋረጥ የተደረገው ብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር መረጃውን እንደማንኛውም ሰው ከኢንተርኔት ላይ ማግኘቱን የገለፁት የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፥ የወጣውን ፈተና ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ዛሬ ማለዳ ላይ ፈተናው እስከሚከፈት እና ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ካለው ፈተና ጋር አመሳክሮ ማረጋገጥ በማስፈለጉ ነው ብለዋል።

ሌሎች ፈተናዎች ላለመውጣታቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ ሁሉም ፈተናዎች መቋረጣቸውን አመልክተዋል።

በመላው ሃገሪቱ 800 የፈተና ጣቢያዎች መኖራቸውን በማንሳት በቀጣይ በየትኛው ጣቢያ ላይ ይህ ፈተና እንደወጣ የምርመራ ስራ እንደሚከናወን ገልፀዋል።

ፈተና ሲዘጋጅ የመጀመሪያ እና መጠባቢያ እቅዶች ማለትም "plan A" እና " Plan B "እንዳለ ያነሱት ሚኒስትሩ፥ የመጀመሪያው በመቋረጡም ሚኒስቴሩ የመጠባበቂያ እቅዱን ማለትም " Plan B " እንደሚተገብር አስታውቀዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የሎጅስቲክ አቅርቦት እንደተሟላ ፈተናው እንደሚሰጥም ነው ሚኒስቴሩ ያመለከተው።

ለመላው ተፈታኞች እና ቤተሰቦቻቸው ይቅርታ የጠየቀው ሚኒስቴሩ ተማሪዎች ወደ ጥናታቸው እንዲመለሱም አሳስቧል።

ከዚህ ቀደም የ10ኛ ክፍል ፈተና ወጥቷል የሚለው ግን ፍፁም ሀሰት መሆኑን ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው አረጋግጠዋል።

በሀብታሙ ገደቤ

- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/news/item/16336-%E1%88%B0%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8B%9C%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%8A%A8%E1%8D%8D%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%89%B5%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8C%8D%E1%89%A2%E1%8B%AB-%E1%8D%88%E1%89%B0%E1%8A%93-%E1%89%B0%E1%88%AB%E1%8B%98%E1%88%98.html#sthash.9upjvpBh.dpuf

No comments:

Post a Comment