Thursday, May 19, 2016

በሃረሪ ብሄራዊ ሊግና በኦህዴድ መካከል ያለው ሽኩቻ ቀጥሎአል

ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሀረሪ ክልልን በሚመሩት የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ( ህብሊ) እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ( ኦህዴድ) መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ አንዱ ድርጅት የሌላውን ድርጅት አባል ከስልጣን እያነሳ ነው። ሃብሊ ለሁለት ቀናት ባደረገው ግምገማም ድርጅቱ ከሁለት መከፈሉ በገሃድ የታዬ ሲሆን፣ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲወርዱ የሚጠይቁና_የእሳቸው ደጋፊዎች እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ ተሰምቷል።
በእርስበርስ ሽኩቻው የተዳከመ የሚመስለው ሃብሊ፣ ዛሬ ከ4 በላይ አመራሮቹ ከስልጣን ተወግደውበታል። የትምህርት ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙክታር ሳላህ፣ የፕሬዚዳንቱ አጎት የሆኑት አፈ ጉባኤው አቶ ያሲን፣ የፕ/ቱ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ አቶ ካሊድ ሃባል ከስልጣን የተነሱ ሲሆን፣ የፕ/ቱ አማካሪና የጠባቂዎቻቸው ሃለፊ አቶ ባህሩ ደግሞ በፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል፤፡
የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማስተናገድ የተመረጠችው ሃረሪ፣ በኦህዴድና በሃብሊ ባለስልጣናት ሽኩቻ ለወራት ስትናጥ ሰንብታለች።
Source:http://amharic.ethsat.com/%e1%89%a0%e1%88%83%e1%88%a8%e1%88%aa-%e1%89%a5%e1%88%84%e1%88%ab%e1%8b%8a-%e1%88%8a%e1%8c%8d%e1%8a%93-%e1%89%a0%e1%8a%a6%e1%88%85%e1%8b%b4%e1%8b%b5-%e1%88%98%e1%8a%ab%e1%8a%a8%e1%88%8d-%e1%8b%ab/

No comments:

Post a Comment