Friday, January 22, 2016

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ ምልክት ማድረግ ሊጀመር ነው


ጥር ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ወይም ኢንሳ አማካኝነት ሲካሄድ የከረመው የሁለቱን አጎራባች አገራት ድንበር የአየር ላይ ፎቶ ወይም erial photo acquisition የመስራቱ ስራ ለሁለት ሳምንት ከተቋረጠ በሁዋላ፣ ሰሞኑን እንደገና የተጀመረ ሲሆን፣ በድንበሩ ላይ ምልክት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የደህንት መስሪያ ቤት ምንጮች ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰአት በድንበሩ ዙሪያ መሬት ላይ ምልክት የማድረግ በእንግሊዝኛ pre mark ground control points እንዲሁም የካርታ ስራውን ለመስራት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ኢንሳ በአማራ ክልል መንግስት ስም በአርሶ አደሮች የእርሻ እና የግጦሽ መሬት ላይ ምልክት የማድረጉን ስራ ለመጀመር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የአካባቢው ህዝብ እና የወረዳ ባለስልጣናት ምልክት በማስቀመጡ ስራ ላይ ትብብር እንዳያደረጉ የደህንነት ምንጮች ምክራቸውን ለግሰዋል።
የመለያ ምልክቶቹ ከአሸዋ፣ ስሚንቶና ጠጠር የሚሰሩ ሲሆን ፣ 3 ሜትር ቁመት እና 60 ሴንቲሜትር ስፋት ያላቸው በነጭና ጥቁር የተቀቡ ይሆናሉ። የቀለም አቀባባቸውም ነጭ፣ ጥቁር፣ ነጭና ጥቁር የሚሆኑ ሲሆን መሃሉ ነጭ ይሆናል።
ኢንሳ ተመሳሳይ የአየር ላይ ፎቶዎችን በወልቃይት ፣ አብደራፊ እንዲሁም ምእራብ አርማጭሆ አካባቢዎች የሚያነሳ ሲሆን፣ ሰፊ የሆነ መሬት ወደ ትግራይ ክልል በመውሰድ የወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት እንዲጠቀምበት እያዘጋጀ ነው።
የስኳር ፋብሪካው አቮሪንጋ በሚባል የእስራኤል ኩባንያ የሚሰራ ይሆናል።

No comments:

Post a Comment