ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በባህርዳር ማረሚያ ቤት ለሚገኙ እስረኞች ያበረከተውን ፍራሽ ማረሚያ ቤቱ ለፖሊሶች ማከፋፈሉን ምንጮች ገለጹ፡፡ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ አዲስ ፍራሽ በመግዛቱ ያገለገሉትን ፍራሾች እስረኞች የፍራሽ ችግር እንዳለባቸው በማወቁ እንዳበረከተ የታወቀ ሲሆን ፣ እስር ቤቱ ግን ለፖሊሶች እንዳከፋፈለ ዩኒቨርስቲው በማወቁ ቅር እንደተሰኘ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁንና ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል ተብሏል፡፡
በባህርዳር እስር ቤቶች የሚገኙ እስረኞች ፍራሽን ጨምሮ ከፍተኛ የአቅርቦት ችግር እንዳለባቸው የገለፁት ምንጮች፣ አብዛኛዎቹ ፖሊሶች የተሰጣቸውን ፍራሽ እንደሸጡት የፖሊስ ምንጮችን ዋቢ አድርገው ገልፀውልናል፡፡
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment