Monday, October 5, 2015

በቴፒ የሚታየው ውጥረት አለመርገቡን ነዋሪዎች ገለጹ


መስከረም ፳፬ (ኅያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብና የጋምቤላ አዋሳኝ በሆነቸው ቴፒ ከተማ በየጊዜው የሚታየው የጸጥታ ችግር ሰሞኑን እንደገና አገርሽቶበታል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ካለፈው አመት ጀምሮ ከፍ ዝቅ እያለ ሲካሄድ የነበረው ግጭት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ በህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነትም ሰፍቷል። መስከረም 20 ብርሃኑ የተባለ የዩኒቨርስቲ ጥበቃ የተገደለ ሲሆን፣ ለግድያው እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።
ባለፈው አመት የአካባቢው ወጣቶች አስር ቤት ሰብረው በመግባት በርካታ እስረኞችን ማስፈታታቸው ይታወቃል። በተለያዩ ወቅቶች በሚፈጸሙ ጥቃቶችም የፖሊስ አባላትና ወታደሮች ተገድለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላትም በከተማዋ ወጣቶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment