ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች በሚያሳድሩበት ጫና ለተጨማሪ ስቃይ እየተዳረገ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል።
የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ውቤ እንደገለጹት፣ እስክንድርን ከሁለት የቅርብ የቤተሰብ አባላት ውጭ ሌሎች ሰዎች እንዳይጥቁት ተከልክለዋል።
በሃይማኖት አባቶችም ሆነ በጠበቃ እንደማይጎበኝ የገለጸው ጋዜጠኛ አበበ፣ በእስር ቤት ውስጥ የተያዘበት መንገድ አሳሳቢ ነው ይላል፡
በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ የሽብር ወንጀል የተከሰሰው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው አቶ ሃብታሙ አያሌው ታሞ ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል።
የግንቦት ሰባት ድርጅትን ደግፋችሁዋል በሚል የተከሰሱ የአርማጭሆ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው የሽብር ክስ ተከፍቶባቸዋል። የ52 አመቱ አቶ ይላቅ አሸንፍና የ66 አመቱ አቶ አዋጁ አቡሃይ ከአርበኞች ግንቦት7 የጦር መሳሪያ ተቀብለው ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቀስዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ኢሳት አቶ አዋጁ አቡሃይና አቶ ይላቅ መያዛቸውን በወቅቱ ተዘግቦ ነበር።
14ኛው ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ለማየት ለ ጥቅምት 3 ፣ 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment