ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊጉ ለኢሳት በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ግብረሃይል ለኬንያ መንግስት የ131 የኦሮሞ ተወላጆችን ስም በመዘርዘር በሽብረተኝነት የሚፈለጉ በመሆኑ ተላልፈው እንዲሰጡት ጠይቋል። በቅርቡ ኬንያ ውስጥ የደረሱበት ያልታወቁት የ80 አመት አዛውንቱ አቶ ደባሳ ጉዮ፣ ከ35 አመታት በላይ ከኖሩበት ኬንያ ታፍነው መወሰዳቸውን ገልጿል። ድርጅቱ የኬንያ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ላቀረበለት ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጥ ጠይቋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የኦሮሞ ስደተኞች ለገጠማቸው አደጋ ትኩረት እንዲሰጡም ድርጅቱ አሳስቧል።
No comments:
Post a Comment