Friday, September 25, 2015

“የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ይችላል” ተመድ


በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ለምግብ እርዳታ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥርና የእርዳታ መጠን በቀጣዮቹ አራት ወራቶች በከፍተኛ መጠን ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስታወቀ።
የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 4.5 ሚሊዮን አካባቢ እንደነበር ያወሳው ድርጀቱ፣ የተረጂዎችን ቁጥር ከታህሳስ ወር መጨረሻ ጀመሮ ጭማሪን እንደሚያሳይ ገልጿል።
በፈረንጆቹ አዲስ አመት ባሉ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች አሁን ያለው የ 151 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ፍላጎት ወደ 237 ሊያሻቅብ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአስቸጓይ ጊዘ የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በወርሃዊ ረፖርቱ አመልክቷል።
በአፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያና፣ ደቡብ ክልሎች የሚገኙ በርካታ ዞኖች የእርዳታ አቅርቦቱ ከሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ዋንኞቹ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት የምግብ እጥረቱን ለመቅረፍ በቂ ክምችት አለ ቢልም ሰሞኑን ለተረጂዎች የአስቸኳይ ጊዘ የምግብ እርዳታ እንዲቀርብለት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።
የበጋ ወቅት ተጠናክሮ መቀጠል በሚጀምር ጊዜ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድና ቁጥሩም አሁን በትክክል ሊታወቅ እንደማይችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመልክቷል።
በአሁኑ ሰዓት ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ወደ አምስት ሚሊዮን ሰዎች የሚያስፈልገው የእርዳታ ገንዘብም እስከ ህዳር ወር 2008 ድረስ መገኘት እንዳለበት ድርጀቱ የገለጸ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ አደጋም የቅርብ ከትትል እንደሚያስፈልገው አስታዉቋል።
በተለያዩ ክልሎች የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ተከትሎም በምግብ ዋጋዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ነዋሪዎችን ይገልጻሉ።
ባለፈው ወር የኢትዮጵያ የምግብ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪን በማሳየት 14.7 በመቶ የዋጋ ግሽበት ማስመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ ማድረጉም ይታወቃል።
Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment