Monday, September 21, 2015

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር 2 ከፍተኛ አመራሮች በአልሸባብ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ * ግንባሩ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ አለበት ሲል ከሰሰ


(ዘ-ሐበሻ) የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ሁለት ከፍተኛ አመራሮቼ ከሶማሊያ ባይዶዋ ወደ ኦጋዴን ሲጓዙ በአልሸባብ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ተገደሉብኝ ሲል ከሰሰ። ለዚህም ተጠያቂው በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ብሏል::

የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከቅርብ ወራት ወዲህ በጠቅላላው ከአስር የማያንሱ አባሎቼ ሶማሊያ ውስጥ በአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ አንገታቸው ታርዶ ተገድለውብኛል ብሏል ።

እንደ ግንባሩ ክስ ከሆእ የኢትዮዽያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች በስውር ከአልሸባብ ንዑስ ቡድን ጋር በመገናኘት ግድያው እንዲፈፀም አሲረዋል።

በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ አገዛዝ እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም መንግስት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ድርጅት ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል:: አማጺው ቡድንም ሆነ መንግስት እርስ በራሳቸው ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው እየተባባሉ መካሰሳቸው ለብዙዎች ግርምታን ፈጥሯል;;

Source:: Zehabesha

No comments:

Post a Comment