Friday, August 21, 2015

በኦሮምያ ደቡብና ሶማሊያ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የማንበብና የመጻፍ ክህሎት ከዜሮ በታች ነው


ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል በሚተገበረው የክላስተር ፖሊሲ በተለይ በኦሮምያ ፤ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የማንበብ እና የመፃፍ ክህሎታቸው ከዜሮ ነጥብ በታች መሆኑን ከትምህርት ሚኒስትር የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡ የተማሪዎቹ የሂሳብ ማስላት ችሎታ መዳከሙን፣ በሳይንስ ትምህርት ላይ ለውጥ እንዲመጣ የተጣለው ግብም አለመሳካቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
መምህራን በትርፍ ጊዜያቸው ጥምር የቲቶሪያል ድጋፍ እየሰጡ ባደረጉት ጥረት መጠነኛ መሻሻሎች ታይተዋል ቢልም፣ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያገኙት የትምህርት ጥራት እንደወደቀ ነው።
ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ ይህንን ችግር ለመቅረፍ 652 ትምህርት ቤቶች ወደ ሙሉ ሳይክል በማሳደግና 146 ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለመቅረፍ እየተሞከረ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በመላ ሐገሪቱ ከሚገኙ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፕላዝማ ቴሌቪዥን ያላቸው 15 ብቻ ሲሆኑ፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እና የተማሪዎች የአቅም ልዩነት የፕላዝማ ትምህርትን ውጤታማ ሊያደርገው አልቻለም ተብሎአል።
በሌላ በኩል በአማራ ክልል ብቻ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ወጣቶች የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ በሆነ ትምህርት ሰልጥነው ያለ ስራ ቤታቸው ተቀምጠዋል፡፡
የክልሉ ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዝማም አሰፋ ወጣቱ በስራ አጥነት ውስጥ ነው ይላሉ። ስራ ፈጣሪ ለመሆን የመልካም አሰተዳደር እና የመንግስት ቢሮክራሲ እንቅፋት ሆኖበታል ሲሉ አክለዋል።

Source : Esat

No comments:

Post a Comment