ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። ከታሰሩት መካከል 6 ያክሉ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ እቅድ ተይዞ በነበረበት በቱሉ አወሊያ አንድ ፖሊስ ተደብድቦ አቀስታ ሆስፒታል ገብቷል።
በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ወጣቶችን ከቤታቸው እያወጣ መደብደቡን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ የጋሞን ህዝብ የሚያንቋሽሽ ጽሁፍ መጻፉን ተከትሎ የተነሳው ውዝግብ እስካሁን አልበረደም። የአካባቢውን የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከሁለት የከፈለውን ውዝግብ ለማብረድ ፣ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የተመራ ቡድን የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ቢያስታውቅም፣ ችግሩ ሊበርድ እንዳልቻለ የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተቃውሞው እንዲሰፋ ከጀርባ ሆነው ግፊት ያደርጋሉ የተባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ከትናንት ጀምሮ ተይዘው ታስረዋል።

Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment