ዛሬ ነሐሴ 13/2007 ዓም 4 ፡ 00 አካባቢ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል
ያለፈው ቀጠሮ ታዞ የነበረው 3ኛ ተከሳሽ መለሰ መንገሻ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) ነህ ተብሎ ለቀረበበት ክስ አባል አይደለሁም ነህ ተብዩ ብከሰስ እንኳን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ያልተፈረጀ ድርጅት በመሆኑ በሽብር ልከሰስ አይገባኝም ብሎ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር ፍርድ ቤቱም የመለሰ መንገሻ ክስ ተነጥሎ በህገመንግስቱ መሠረት ተሻሽሎ ይቅረብ ሲል አዞ ነበር
አቃቤ ህግ ግን በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት ክሱን አሻሽሎ ባለማቅረቡ ድጋሚ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቇል ፍርድ ቤቱም ለጥቅምት 12/2008 ዓም ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ አንዲያቀርብ አዟል
ዘመነ ምህረት አፍተኛ ድብደባ ተፈፀመበት
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ም/ል ፕሬዝደንት ዘመነ ምህረት በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ሀላፊዎች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመበት
ከወራት በፊት በአግአዚ አባል እንገድልሃለን የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሠብኝ ነው ለህይወቴ እሰጋለሁ ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ ብሎ አቤቱታ አቅርቦ ነበር ሠሚ ግን አላገኘም ነበር
ያለው አልቀረም በ11/11/2007 ዓም ሌሊት ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበታል
የቅሊንጦ እስር ቤት ሀላፊዎች በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የምትለፈልፈውን አቁም ብንልህ ልትሠማ አልቻልክም ፍርድ ቤቱ የኛ እንደሆነ አታውቅም ማን የሚያድንህ መሠለህ እያሉ ዘቅዝቀው በክላሽ ሠደፍ እና በሳንጃው እንደቀጠቀጡት በድብደባው እጁ በከፍተኛ ደረጃ እንደተጎዳ እግሩም በጣም እንደተጎዳ ገልጿል እኛም መጎዳቱን ፍርድ ቤት ሲገባና ሲወጣ መራመድ አቅቶት ተመልክተናል ቀደም ብየ ይህ እንደሚደርስብኝ አውቄ ነበር እዚህ ችሎት ላይ አቅርቤ ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ባለመስጠቱ ነው የተፈፀመብኝ እያለ ሲያቀርብ የስርአቱ አሽከር የሆነው ፍርድ ቤት ተፈፀመብኝ የምትለውን በጽሁፍ አቅርብ ብሎታል ዘመነ ግን ህይወቴ አደጋ ላይ ነው በማለት የተደበደበውን አሳይቷል ዳኞቹ ግን ከቁብም አልቆጠሩት ዝም አሉ እንዳይባል ብቻ
እነ ዘመነን አጅበው ያመጡትን ፓሊሶች ዘመነ ባቀረበው አቤቱታ ላይ መልስ እንዲስጡ ጋብዟቸው ነበር ፓሊሶቹ እኛ አጅበን ከመምጣት ውጭ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ተፈፀመብኝ ስላለው ድብደባ የምናውቀው ነገር የለም ይህንን ጉዳይ መልስ መስጠት ያለበት ማረሚያ ቤቱ ነው ብለዋል
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ዘመነ ምህረት ባቀረበው አቤቱታ ላይ ጥቅምት 12/2008 ዓም ማረሚያ ቤቱ መልስ እንዲሰጥ ሲል አዟል :
Source :https://m.facebook.com/jomanex/posts/10206962620041941
No comments:
Post a Comment