አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ግንባሮች በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት ተከትሎ ከወያኔ ጎራ የተምታቱ ዜናዎች እየተደመጡ ነው።Ethiopian PM Hailemariam Desalegn on Al Jazeera
ቀደም ሲል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት “ምንም ነገር የለም” ብለው ለማድበስበስ የሞከሩት የወያኔ ሹማምንትና ካድሬዎች ዜናው በኢሳት ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና በዋንኛነት ደግሞ በማህበራዊ መገናኛ ገጾች በስፋት በመዘገቡ “ምንም ነገር የለም” ከሚለው ወደ ተምታታ ዜና ማሰራጨት ተሸጋግረዋል።
የወያኔዎቹ ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳ በሚሚ ስብሃቱ ኤፍ ኤም ራድዮ ላይ ቀርቦ “በአካባቢው በመሬት የተነሳ መጠነኛ ግጭት ነበር” በማለት ሁኔታውን ከገለጸ በኋላ ወድያውም “በሻብያ ላይ የማያዳግም ቅጣት” ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ተናግሯል።
አይጋ ፎረም የሚባለውና በአፍቃሪ ወያኔነቱ የሚታወቀው ድረገጽ ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ በሻብያ ተላኩ ያላቸውን ታጣቂዎች መማረኩን ዘግቧል።
አነጋጋሪ የሆነውና ምናልባትም አብዛኞችን ፈገግ ያደረገው ዜና ደግሞ ኣሻንጉሊቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአሻንጉሊቱ የተወካዮች ምክር ቤት ያደረጉት ንግግር ነው፣ “ህዝብን አስፈቅደን ከሻብያ ጋር ጦርነት እንገጥማለን” ነበር ያሉት ኃይለማርያም ደሳለኝ።
የወያኔ ሹማምንት ጥቃት እየሰነዘረባቸው ያለውን “አርበኞች ግንቦት 7ን” በስም ለመጥቀስ እጅግ የፈሩ ይመስላሉ።
አርበኞች ግንቦት 7ን በስም መጥቀስ ለምን ፈሩ? ብሎ ለሚጠይቅ መልሱ ቀላል ነው።
ህዝብ የአርበኞች ግንቦት 7 የነጻነት ታጋዮች ከአብራኩ የወጡ የቁርጥ ቀን ልጆቹ እንደሆኑ ያውቃል። ስለዚህም ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ጦርነት ልንገጥም ነው ቢሉ ማንም እንደማይተባበራቸው ይረዳሉ። ያላቸው እድል “ሻብያ” እያሉ መለፈፍ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ይገነዘባል ይሁንና የወያኔ አስከፊ ዘረኛ ስርዓት እያደረሰበት ካለው የመረረ ጭቆና ጋር በማነጻጸር ይመስላል አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የሰነዘረውን ጥቃት በደስታ ነው የተቀበለው።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢሳት ቴሌቭዥን በመደወል ደስታቸውን ሲገልጹና ለአርበኞቹም መልካሙን ሁሉ ሲመኙ ተደምጠዋል።
No comments:
Post a Comment