Thursday, July 23, 2015

በባህርዳር የቀድሞ የሰራዊት አባላት ያደረጉት ተቃውሞ በሃይል ተበተነ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው መንግስት ዘመን በውትድርና ሙያ አገራቸውን ያገለገሉ እንዲሁም በኢህአዴግ ዘመን በተመሳሳይ ሙያ ያገለገሉ እና ያለ ስራ ወይም ያለጡረታ የተሰናበቱ ወታደሮች፣ በአገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት መቋቋም አልቻልንም፣ መንግሰት ስራ ይሰጠን ወይም ደሞዝ ይክፈለን በሚል የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመነሳት ወደ መስተዳድሩ ጽ/ቤት በማምራት ላይ የነበሩ ወታደሮች ፣ መስተዳድሩ አካባቢ ሳይደርሱ በፌደራል ፖሊስ እንዲበተኑ ተደርጓል። በፖሊሶችና በቀድሞ ወታደሮች መካከል መጠነኛ የሆነ ግጭት ቢነሳም፣ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ ሰልፉ ተበትኗል።
ወታደሮቹ ለሱዳን የተሰጠው መሬት ህገወጥ ነው በማለት ሲያወግዙም ተሰምተዋል። በአገራቸው የመስሪያ መሬት አጥተው፣ የአገሪቱ መሬት ለሱዳን እየተቆረሰ ይሰጣል በማለት አገዛዙን ሲያወግዙ እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment