ህዝቡ አሳልፎ ለፖሊስ የሰጣቸውና ለኢትዮጵያ መንግስት ይሰልሉ እንደነበር ከተነገረባቸው ሰዎች መካከል በአንዱ እጅ ሶስት የእጅ ስልኮች፣ፖሊሶች የሚይዙት መገናኛ(ዎኪ ቶኪ)እንዲሁም በአንደኛው ተጠርጣሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከሰባ የሚልቁ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ስምና ብዛት ያላቸው ፎቶ ግራፎች መገኘታቸውን በወቅቱ ካነጋገርኳቸው ሰዎች ለመረዳት ችያለሁ፡፡የኬንያ ፖሊስ ግለሰቡን በኢትዮጵያ ኢምባሲ ዋስትና መልቀቁን የሚጠቅሱ በአገሪቱ የሚኖሩ ስደተኞች እንዲጠነቀቁት ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ከኬንያ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ በኢትዮጵያ በተደረገበት ማሰቃየት ለሞት መዳረጉን በምሬት የሚያስታውሱት ስደተኞቹ ‹‹ በኬንያ ባልታወቁ ሰዎች ተገድለው የሚገኙ ወገኖቻችንና ከዚህ ታፍነው እየተወሰዱ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች በመሰቃየት ላይ ስለሚገኙ ሁሉ ፍትህን ከመጠየቅ ለአፍታ አናመነታም፡፡ብለዋል፡፡
Source: https://www.facebook.com
No comments:
Post a Comment