Tuesday, June 16, 2015

በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው


ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትሪፖሊ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት ሰሞኑን እንደ አዲስ በተጀመረው አፈሳ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ
እስር ቤቶች ከ500 ያላነሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በህወጥ አዘዋዋሪዎች ሲሆን፣ ገንዘብ ካላመጡ እንደማይለቀቁ እንደሚነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት ሲናገር፣ በእስር ቤቱ ውስጥ ዱላ የቀን ተቀን ህይወት ነው፣ ኢትዮጵያውያኑ በዱላ ብዛት
አካላቸው እየጎደለ ነው ብሎአል። አንድ እርጉዝ ሴት በበኩሏ ተይዛ ገንዘብ ከፍላ መለቀቋን ገልጻለች።
መንግስት ሊቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገር እየመለስኩ ነው ቢልም፣ ኢትዮጵያውያኑ ግን “ግብጽ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስንደውል አግኙት ተብሎ የሚሰጠን ሰው ስልክ ፣ ‘ፓስፖርት ይዛችሁዋል?’ እያለ ይቀልድብናል፣ ገንዘብም
ይጠይቀናል” በማለት እየረዳቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል።

source: http://ethsat

No comments:

Post a Comment