Wednesday, May 6, 2015

በቅርቡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታሰሩት ወጣቶች በሃሰት እንዲመሰክሩ ጫና እየተደረገባቸው ነው


ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ለመዘከርና ቁጣቸውን ለመግለጽ ገዢው ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወጣቶች መንግስትን ሰድባችሁዋል በሚል ታፍሰው ከታሰሩ በሁዋላ፣ “ተቃውሞውን
ያስነሱት በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ናቸው” ብላችሁ ካልመሰከራችሁ አትለቀቁም መባላቸውን የእስረኞች ቤተሰቦች ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ወጣቶች ማታ ማታ በደህንነት ሃይሎች እየተጠሩ በታሰሩ የሰማያዊ አባላት ላይ እንዲመሰክሩ ጫና እየተደረገባቸው ነው።
ወላጆች ልጆቻቸው በንጹሃን ላይ በሃሰት እንዳይመሰክሩ እንደመከሩዋቸው ተናግረዋል። ህዝቡ በኑሮውና በፍትህ እጦት ተማሮ በራሱ ጊዜ ተቃውሞውን ቢያሰማም፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ያስነሳው ሰማያዊ ፓርቲ ነው በማለት እየወነጀለ ነው። የገዢውን ፓርቲ ውንጀላ
አባሎቹ ሳይቀሩ አልተቀበሉትም።

No comments:

Post a Comment