Thursday, May 7, 2015

*** በግብጽ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሊቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እርዳታ ሲሹ እንዲደውሉ ያሰራጨው ስልክ ቁጥር የሕገ-ወጥ ደላሎች ስልክ ቁጥር ሆኖ እንደተገኘ በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ለኢሳት ገለጹ። መረጃቸውን በድምጽ አቅርበዋል።





***በሜዲተራኒያን ባህር 700 ሰዎችን ይዞ በሰጠመው እና ከ30 የማይበልጡ በተረፉበት አደጋ ኢትዮጵያዊያን መሞታቸው ተሰማ። ኢሳት ያነጋገራችው ቤተሰብ ከጉዞው አንድ ቀን በፊት ስልክ ደውሎ "ወደ አውሮፓ ነገ እሄዳለሁ" ብሏችው ከዚያ ቀን በኋላ ዳግም ድምጹን እንዳልሰሙት ተናግረዋል።
***በእስራኤል ዘረኛነት እና መድልዎ ያንገሸገሻቸው ኢትዮ-አይሁዳዊያን እና በስደት ያሉ ኢትዮጵያዊያን በቴላቪቭ እና በእየሩሳሌም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በእስራኤል ያለው ችግር ምንድነው? በቅርቡ በሀገሪቷ በተካሄደ ምርጫ የሊኩድ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው የፓርላማ ወንበር ያገኙት ትውልደ-ኢትዮጵያዊ ዶክተር አብረሀም ንጉሤ ይተነትናሉ። በነጭ የእስራኤል ፖሊሶች ከተደበደበው ደምስ ፈቃደ ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤንያሚን ኔታኒያሁን አግኝተዋል። ኔታንያሁ ምን አሉ?

No comments:

Post a Comment