Wednesday, May 6, 2015

ፌደራል ፖሊስ በማእከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት እስረኞች እርስ በርስ እንዲወነጃጀሉ እያደረገ ነው


ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ታህሳስ ወር አርበኞች ግንቦት7ትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ መንገድ ላይ ተይዘዋል ባላቸው እሰረኞች ላይ ለደረጃ ምስክርነት አብረው ከታሰሩት መካከል እያሰለጠ ነው።
አንዳንዶች ፖሊስ ራሱ ያዘጋጀውን ቃል በፍርድ ቤት ተገኝተው የሚሉ ከሆነ ከእስር እንደሚፈቱ ፣  ለመመስከር ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ እድሜ ልካቸውን በእስር ላይ እንደሚቆዩ እንደተነገራቸው ምንጮች ገልጸዋል።
ሰለሞን አሞኘ የተባለው እስረኛ በፈረጃ አሞር ላይ እንዲመሰክር እየሰለጠነ ሲሆን፣ መንግስቱ  መላክ፣ ሃብቱ ጫቅሉና ሃብቴ አምባቸው ደግሞ  አምላኩ መስታወት ላይ ይመሰክራሉ። በእነ አምላኩ መዝገብ 6 ሰዎች የሚገኙ ሲሆን፣ እስካሁን በማእከላዊ ስቃይ እየደረሰባቸው ይገኛሉ።
በእነ መምህር ደሴ ላይ ደግሞ ወታደር ደሴ እንዲሁም በመምህር አደረጃውና ጥላሁን ላይ ደግሞ ተስፋየ ተፈሪ ለምስክርነት እየሰለጡኑ  ነው።
እስረኞቹ ማይካድራ ላይ መያዛቸው መዘገቡ ይታወሳል። ገዢው ፓርቲ መስክሮችን ማግኘት ባለመቻሉ፣ እስረኞች አንዱ በሌላው ላይ እንዲመሰክር በማድረግ እርስ በርስ እንዲጣሉ በማድረግ ላይ መሆኑን የማእከላዊ ምንጮች ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment