ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ ፕሬዚዳንት እስማዔል አሊ ሴሮ እና በጸጥታ ዘርፍና በፍትህ ቢሮ ሃላፊው መካከል የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ ተባብሶ በወረዳ ያሉ አመራሮችን ሳይቀር መከፋፋሉንየኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ አሊ ሴሮ ከ24 አመት በላይ የያዙትን የፕሬዚዳንትነት ቦታ በሚቀጥለው አመት እንደሚለቁ ፍንጮች መታየታቸው አሁን ለታየው የስልጣን ሽኩቻ መንስኤ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ አሊ ሴሮ ለእርሳቸው ቀረቤታ ያላቸው አቶ አወል አርባ ቦታውን እንዲይዙ የሚፈልጉ ቢሆንም፣ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው አቶ ስዩም አወል ደግሞ ራሳቸውን ታማኝ ሰው ማስመረጥ ይፈልጋሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ገአስ አህመድ አቶ እስማኤል ባለፉት 24 አመታት ለፈጸሙት ከባድ ወንጀል እንዳይጠየቁ ለማድረግ የራሳቸውን ሰው ለማስቀመጥ መወሰናቸውን ገልጸው፣ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግን ይህን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆኑና አቶ እስማኤል ለክልል ምክር ቤት እንዳይመረጡ ግፊት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ከአቶ ገአስ አህመድ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለምልልስ ከዜናው ቀጥሎ ይቀርባል።
source:ethsat.com
No comments:
Post a Comment