Saturday, December 10, 2016

የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ – ታሪኩ ውብነህ ጌታሁን

ክፍል አንድ
ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ
[ማሳስቢያ፡ ይህ በክፍል አንድ የቀረበው ጽሑፍ ለማሰተማር ሳይሆን ለመማማር ታስቦ መሆኑን ለአንባቢ ማሳወቅ እወዳለሁ፤ስለኢትዮጵያ የሚጻፉትን የምችለውን ያህል እከታተላለሁ፤ነገር ግን እጅጉን ያስቸገረኝ ጸሐፊዎች ስለ አሁን አለንበት “ሁኔታ” ሲጽፉ እንደመሰላቸው ብቻ ሳይሆን የአንባቢዎቻቸዉን ችሎታ ከግንዛቤ ሲያሰገቡ መሆኑን  ጽሑፋቸው በሚገባ ያንፅባርቃል፤ለዚህም በመረጃነት የማቀርበው ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ሊቃን አሁን ባለው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የጻፉትን በመመልከት ነው፤ እንዲት እንደተመለከትኩት በአጭሩ ላስረዳ፤ ከአንድ ወዳጄ ጋር በቅርቡ ታትሞ ስለወጣ መጽሐፍ ስናወራ “ጸሐፊው ዝም ብሎ ነው፤ከዚህም ከዚያም አሰባስቦ መጽሐፍ ጻፍኩይላል” አለኝ፤ መጽሐፉ በሚገባ ስለተጻፈ ሁለት ግዜ አንብቤ ያደነቅሁት ጽሑፍ ነው፤ ስለዚህ ይህንን ወዳጄን መጽሐፉን ማንበቡን ጠየኩት፤መልሱ በጣም የሚያስገርም ነው፤መልሶም “ለምንድነው ከዚህም ከዚያም የተለቃቀመ ጽሑፍ የማነበው” አለኝ፤ እዚህ ላይ ስለመጻሕፋ ውይይት ቆመ፤ ምክናያቱም እኔ እንደገባኝ “ያለማውቅ እንዲት ደፋር እንደሚያደርግ” እና ሊላዉንም እንዲት ደፋር እንደሚያደርግ ስለ አስረዳኝ ነው። ይህ ወዳጄ መጽሐፉን ቢያነበው ኖሮ ተወያይተን እንማማር  ነበር፤ ማጋነን አይሁንብኝምና ይህ ወዳጄ እስክማውቀው ድረስ አንድ መጽሐፍ አንብቦ አያውቅም፤ አንብቦማ ቢሆን መጽሐፍ የሚጻፈው የተለያዩ ጽሁፎቹን አንብቦ ነው፤ የተለቃቀሙት ጽሑፎች ከብዙ መጻሕፍት ሲሁኑማ የጸሐፊው ዕውቀት በዚያው ልክ ክፍ ይላል።  ስለ ጽሑፍ መለቃቀም ታላቁ የኢትዮጵያ ፈላስፋ የጻፈዉን በማስታወስ ነው፤ ፈላስፋው ዘርዓ ያዕቆብ (ንጉሡን አይደለም) ንቧ የምታደርገዉን ተገንዝቦ እንዲህ ይላል፤ “ንቧ የተለያዩትን አበባዎችን ቀስማ ማሩን ታመርታለች፤ ማሩም ጥሩ ማዕዛ የሚስጥ መጠጥ ይሆናል፤የመጠጡም ቅሪት ጧፍ ሆኖ በጨልመ ግዜ ብርሃንን ይሰጣል” ይላል፤ ይህ ፕሮፊሰር መሳይ ከበደን ያስቆጣል፤ምክናያቱም ዘርዓ ያዕቆብን ፈላስፋ ነው ብለው አይቀበሉትም፤ የዘውግ አቀኝቃኝ ስለሆኑ አፍሪቃዌ እንደ አውሮፓውያን ፈላስፋ ይሆናል ብለው ስለሚያምኑ፤ ሆኖም ጽሑፋቸዉን በሚገባ አጥንቺአልሁ፤  የኢትዮጵያ ታሪክና የፖለቲካውን ሥርዓት አዋቂ ስለተባሉት ረኔ ለፎርት ለማወቅ ብዙ ጥረት አድርጌአለህ፤ ነገር ግን ምንም ያገኝሁት ነገር የለም፤ ስለዚህ የምሰጠው አስተያየት ሁለቱ በአደረጉት ውይይት ላይ ብቻ ይሆናል፤ የዚህ ጽሑፍ ዋናው አላማው ከአንባቢ ጋር ለመወያየትና ለመማማር ስለሆነ የጽሑፉን ይዘት ከመረጃ ጋር እንመለከታልን፤ እዚህ ላይ መጠንቀቅ የሚያስፈልገው ውይይታችንን አቅጣጫ እንዳይዝ የሚደረገዉን ጥረት መቛቛም ይኖርብናል፤ እንግዲህ ውይይታችን ረጅም የሆነ “ታሪካዌ ሂደት” ስለሆነ አስፈላጊዉን ግዜ ወስደን መወያየት አስፈላጊ ነው፤ “ከታሪክ የማይማር ውጢቱ ሞት ነው” እንደተባለው ሁሉ እኛም ያለፈዉን ስህተት እንዳንደግም አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ አልብን፤ አዶልፍ ሒተለርና ዱቼ ሙሶሎኒን መቋቋም ሲገባቸው ዝም ያሉ ሰዎች የደረሰባቸው ሞት ነበር፤ በእነዚህ ሁለት እብዶች ምክናያት 100 ሚሊዮን ሕይወታቸዉን አጥተዋል፤ ወያኒ ትግሪ በላይ ከአልሆነ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አይኖርም እያለ እሱን አዝሎ እሽሩሩ ማለት መጨረሻው ሞት ነው፤ይህ ጽሑፍ በብዙ ክፍል ተከፋፍሎ ይቀርባል፤ በመጨረሻም ትንታኔ ይሰጣል፤ አንባቢን ለማዘጋጀት ያህል የምናደርገው ትንታኒ በቀረቡት ጽሑፍ ላይ ይሆናል፤ ለምሳሊ (በግእሊዘኛ content analysis on: “the outgrowth of the success of the ruling party; strong economic growth; the creation of demanding society; distribution of its benefit; Pragmatic leadership; they are obsessed with the wellbeing of Ethiopia; relied on a high economic growth and a drastic change or reform). እነዚህ ከጽሑፋቸው ላይ ቀንጠብ ተደርጎ የተወሰዱ ናቸው፤ የዘር ማጥፋት በከፍተኛ ደረጃ እየተካሀደ፤ የአገር መሪት በጅምላ እየተሽጠ፤የሰው ልጅ ሰብአዌ መብቱ ተገፎ እንደ ሰው የማይታይበት ሁኒታ ተፈጥሮ፤ይደረጋል ተብሎ የማይታሰብ ነገር እየተደረገ ወንበዲዎችና ወንጀለኞችን የሚሻሻሉብትን ዘዴ መፈልግ አጋባብ ያለመሆኑን ተረድተን በአንድ ነት አገራችንን የምናድንበትን መንገድ መከተል ይኖርብናል፤የኢትዮጵያ ሕዝብ አልፎን ሂዷል፤ የጎበዝ አለቃዉን እየምረጠ ነፃነቱን አውጇል ባሁኑ ስዓት ብሒራዌ ሽንጎ የሚመርጥበትን መንገድ ማሳየትና መንግሥቱን እንዲት እንደሚያዋቅር እርዳታ  መስጠት እንጂ ከባሕር ማዶ ሆኖ የግል አስተያየቱን ማስተጋባት ግዚው አልፎቦታል። የሚመጣው መንግሥት በሕዝብ ለሕዝብ ይሆናል። መልካም ንባብ]
እነዚህ ሁለት አንጋፋ ሊቃን ታሪክ ታሪክን ይደግማል የሚባለውን እውን መሆኑን ሊያሰረዱ የተካኑ ምሁራን ይመስላሉ፤ አንዱን በሚገባ አውቃችዋለሁ፤ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በሙያቸው የዘውግ ፍልስፍና [ethno-philosopher] ሊቃን ናቸው። አቶ ሬኔ ለፎርት [Rene Lefort] ማን እንደሆኑ የሰማሁት ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በአድናቅት የኢትዮጵያን ታሪክ አዋቂና የወቅቱን የአገር አስተዳደር በሚገባ የሚያውቁ ሊቃን መሆናችዉን በጽሑፋቸው ላይ ከአነበብኩ በኃሏ ነው። እንግዲህ ይህ ከተባለ በኃሏ የራሴን ሙያ በመጠኑ ማሳወቅ ግዲታ ነው፤የታሪክና የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት ተማሪ ነኝ። ምንም እንኳ የተጠቀሱትን ትምህርት ጨርሼ በአጠናቅቅም መማሬን አላቆምኩም፤ አሁንም እየተማርኩ ነው፤ የነዚህ ትምህርት ክፍል ሰፌ ስለሆነና ግዜዉን እየጠበቀ ስለሚለዋወጥ ማሊቂያ የለዉም። ታሪክም የፖለቲካ ሥርዓትም “ሁኒታ” ይለዉጣችዋል፤ መደበኛ ወይም አይነተኛ አቋም የላቸዉም። የሁኒታ ተገዥ ትዕይንት ናቸው። “ሁኒታ” ይፈጠራችዋል ደግሞም “ሁኒታ” መልሶ ያጠፋችዋል። ይህንን እንደመግቢያ ከአልኩ በኃሏ ወደ እርዕስቱ እገባለህ።
በመጀመረያ ከላይ የተጠቀሰው አርዕስት የተመረጠበት ምክንያት የእነዚህ ሁለት ሊቃን በኢትዮ-ሚዲያ [ethiomedaia-11/26/16 and 12/5/16] በአደረጉት ውይይት ላይ የተመሰረተ ነው። ውይይታቸው ጥሩ ነው፤ከዘያም በላይ ደገሞ የሚያሳየው መከባበርን ነው፤ከዚያም አልፎ  አንዱ የሊላዉን ዕውቀት ታላቅና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ነው፤ ይህንን መልካም አስተያየት  ማንም አይቃወምም፤ ለአንድ አገር በጎ መመኞት ያስመሰግናል፤ይህንን በጎ አስተሳሰባቸወን እያመሰገንኩ ውይይታቸው የኢትዮጵያ ታሪክ አይደለም፤ አሁን ከአለውም የፖለቲካ ሥርዓት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ ስለዘህ ከላይ የተጠቀሰው እርዕስት “የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ” መባሉ ትክክል መሆኑን ለአንባቢ ማስረዳት ግዲታ ነው። በይበልጥ አንባቢ መረዳት ያለበት አሁን  ያለው ሥርዓት ሁለቱ ሊቃን እናዳወጉት ወግ ሳይሆን  ማየት ያለብን ታሪካዌ ሄደቱን ነው። እነሱ እንዳወጉት ወግ የፖለቲካ ሥርዓት ተሽላልሞና ተቀባብቶ ሊሻሻል የሚችል የመንግሥት መዋቅር አይደለም። የሥርዓቱ ታሪክ እንዳወጉት ወግ ሳይሆን ራሱን የቻለ የታሪክ አምድ አለው። ይህንን መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ ግዲታ ነው። ከታሪክ አምድ ከመጋባቴ በፊት የኢትዮጵያን ታሪክና የአገሩን የአስተዳደር መዋቅር በሚገባ ያውቃሉ የተባሉት ሊቃን ሬኔ ለፎርት ስለ ፖሮፌሰር መሳይ ከበደ ለሰጡት ምስክርነት አጠር ያለ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው። ፖረፈሰሩ በአብዮቱ ዘመን አደረጉ ለተባለው መስትዋጽኦ በደርግ ግዜ በቀበሌ ሊቀ መንበርነት ማገልገላቸው የሚታወቅ ነው። ነገር ግን በኢትዮጵያ ሊቃን ዉስጥ ያደረጉት መስተዋጽኦ ቢኖር አንድ ብሒር ሊሎቹን በቅኝ ገዥነት [እሳቸው እንደሚሉት eternal colonization እያሉ መጻፋቸዉን በማስታወስ ነው፤ ይህንን አላልኩም ከአሉ እንደመሻሻል መወሰድ አለበት] ለብዙ ዘመናት አንድ ብሒር ሊሎቹን ብሒረሰቦች ጨቁኗል በማለት ታላቅ መስተዋጽኦ አድርገዋል ከሆነ ትክክል ነው፤ የታሪክ ሊቃኑ ለፎርት ለገዥው አካል ቅርበት አላቸው ስለተባለ የፖሮፌሰሩን የጎሳ/የዘውግ አቅኝቃኝነት ማወደሳቸው መሆኑን አንባቢ መረዳት ይኖርበታል።  ስለዘህ ጉዳይ በመጨረሻ አስተያየት ላይ በሰፊው ይቀርባል። አሁን ለአንባቢ የወያኒን የፖለቲካ ሥርዓት ከየት እንደመጣና ታሪካዌ ሂደቱ እንዲት እንደተመሰረተ አንባቢ ማወቅ ግዲታ ነው፤ ከዚያም አልፎ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ኢትዮጵያዉነታችን የራሳችንን ታሪክ ባለቢት ሆነን ችግራችንን እንድንፈታ በማሳብ በተረጋጋ መንፈስ መወያያት ይኖርብናል። አገራችን ላይ ያለው ችግር በሁለት ሊቃን ወግ ሊፈታ አይችልም፤ ደግሞም እነሱ እንደሚሉት በቀላሉ ሊጠገን የሚችል ሥርዓት አይደለም፤ ይህንንም በአጭሩ ለማስረዳት እሞክራለህ። ይህ ከተባለ በኃላ የአሁኑ ሥርዓት ከየት እንደመጣ እንዴትስ እንደተጀመረ ማሳወቁ ምስቅልቅሉ የወጣዉን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሥርዓትና ታሪካዌ ሂደቱን ማወቁ ለአስተሳሰባችን አቅጣጫ ይሰጣል ብዮ እገምታለሁ። ይህንን ሰፋ ያለ ታሪካዌ ሂደት በቅጡ ይመልከቱት።
የአፍሪቃና የአውሮፓው አህጉር ግንኙነት የጀመረው በ1498 አካባቢ በፖርቲጌስ [Portuuese] መንግሥት በተላከው ቫስኮ ዳጋማ [Vasco da Gama] በሚባለው መርከበኛ መሪነት ነበር፤ መርከበኛው ከአውሮፓ ተነስቶ ወደ ምስራቅ ኢሲያ ሲሂድ በአጋጣሚ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ወደብ ደርሶ እግረ መንገዱን ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ወደብ በመሂድ አውሮፓዉያንን ከአፍሪቃና ከሩቅ ምስራቅ ጋር የሚያገናኝዉን የባሕር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈተ። ይህም ለአውሮፓያን ንግድ ጥሩ አጋጣሚ ነበር፤ በግዜው የነበረው ንግድ ከአፍሪቃና ከኢስያ ጋር ስለነበር አውሮፓዉያን የዚህ ንግድ ተካፋይ ከመሆን አልፈው አካባቢዉን ለመቆጣጠር ጥሩ አጋጣሚ ስለአገኙ ጎሗ በምትባል የሕንድ ከተማ ላይ ምሽጋቸውን በማመቻቸት በምስራቅ አፍሪቃ በሚገኙት ኪ-ስዋሕሊ ተናጋሪዎችና በአረብ ነጋዴዎች ታላቅ የሆነ የንግድ ቅብብልና ውድድር ጀመሩ። ውድድሩ ከፍ ባለ ሁኔታ ስለተካሂደ ሊላ የአውሮፓ አገሮች አዲስ በተከፈተው ባሕር መስመር መምጣት ጀመሩ። ግን ፖርቱጌስ በተቀዳሚነት የምስራቅ አፍሪቃን ወደብን አልፈው  መሐል በመግባት በወርቅ ማዕድን የታወቀችዉን ሾና የምትባለዉን አገር ከሙታምፓ አገረ ገዥ ጋር ስምምነት በማድረግ የወርቁን ማዕድን ተቆጣጥረዉት ነበር፤ በ1659 ዓ ም የፖርቱጌስ መንግሥት ጠቅላላ አገሩን ለመቆጣጠር አስቦ ከፍተኛ የጥር ኃይል ልኮ ነበር፤ ግን የአገሬው ሕዝብ ከመሬው ጋር በመተባበር አገሩን አልሰጥም ስለ አለ የቅኝ ገዥነቱ ሳይሳካ ቀረ፤ ይህ በዚህ እንዳለ  የፖርቱጌስ ቅኝ ገዥነት በመንግሥት ደረጃ መሆኑ ቀርቶ ዜጎቿን ቀስ በቀስ በማስገባት በዴፕሎማሲ የአገሩን መሬዎች እንዲያግባቡ በማድረግና አንዱን መሪ ከሊላው መሪ በማጋጨት፤ መሳሪያ በማቀበልና ዚጎቿን በአባሪነት በማስተባበር የአገር መሪዎችን እንዲተባበሩ በማድረግ የወደፊቱን የቅኝ ገዥነት ዕቅዳቸዉን ከግቡ ለማድረስ ችለዋል። ምንም እንኳ ቫስኮ ዳጋማ  በደቡብና በምስራቅ አፍሪቃ  የነበረዉን የባሕር መንገድ ለአውሮፓዉያን በመጀምሪያ ቢከፍት የቅኝ ገዥነቱ እድል የደረሰው ለደች ምስራቅ [the Dutch East India Company] የንግድ ድርጅት ነበር፤ ይህ የደች ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃን ወደብ አልፎ ወደ ደቡብ አፍሪቃ ወደብ በመድረስ “የወደፊቱ ከተማ ተስፋ በደቡብ አፍሪቃ ወደብ” [the Cape of Good Hope of South Africa] ተብሎ የሚጠራው ወደብ ላይ ምሽጉን አቋቋመ፤ ስለ ስሙ ስያሚ ብዙ አባባል አለ፤ አንደኛው ከሩቅ ምስራቅ ጋር በባሕር ጉዞ ስለአገናኘ የተሰጠው ቅጽል ስም ነው ይላሉ፤እዘህ ላይ የሚደረገው ጥረት አንባቢ የዚህን ታሪካዌ ሂደት በቅደም ተከተል ተከትሎ “ሁኔታ” በመለዋወጥ ያደረገዉን ለዉጥና ያስከተለዉን ጥፋት  ነው። ይህ ከዚህ በላይ የተጻፈው የታሪካዌ ሂደት መቅድም ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ የአውሮፓዉያን ቅኝ ገዥነት እንዲት እንደተስፋፋ በቅደም ተከተል ስለሚቀርቡ አንባቢ በትኩረት መገንዘብ ይኖርብርታል።
  1. የደች ኢስት ኢንድያ ንግድ ድርጅት የደቡብ አፍሪቃን ወደብ ከተቆጣጠረ በኋላ ቀስ በቀስ እየገፋ ወደ ማህል አገር ገብተው ሕዝቡንና አገሩን መቆጣጠር ችለዋል፤ የአገሩ ተወላጅ በተቻላቸው መጠን መዋጋተቸዉን ታሪክ ይመሰክራል፤ ነገር ግን አውሮፓዉያኖች ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ስለነበራቸው የአገሩን ለም መሪት፤ ክብት፤ ማዕድን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግና ከዉጭ ሰራተኞች በማስመጣት የአገሪዉን ሰው በማግለል ኢኮነሚውንና አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የአገሩ ባለቢት ሆነው ነበር፤ ለዚህም መሆን የበቁት በባብርነት ከሲሎን፤ከሕንድ፤ከኢንዶኒሽያ፤ከማልያ፤ከማዳጋስካር በመጡት ሰራተኞች ኃይል ነበር፤ያለምንም ክፍያ በጉልበታቸው ስለአገለገሉ አውሮፓዉያኖች የአገሩን ሰው ለማሽነፍ አስችሎችዋል፤ሆኖም የዙሉ፤የናታል፤የኮሕ ኮሕይ፤ሕዝብ ለነፃነታቸው ብዙ ታግለው መስዋዕት ሆነዋል፤ የደቡብ አፍሪቃ ትግል መራርና አስከፊ ቢሆንም አውሮፓዉያን የነጭ መንግሥት በማቋቋምና የተለያየ ሕግ በማውጣት አውሮፓውያን ያልሆኑትን ብሒረ ሰቦች በማግለል በአፓራታይድ ሥርዕት [Apartheid System: The Native act of 1913]. ለቡዙ ዘመን ገዝተዋል።
  2. የታሪክ ሂደት የሚመዘነው “ሁኔታዉን” በፈጠረው ኃይል ነው፤ ለምሳሊ ፖርቱጌስ በቫስኮ ዳጋማ መሪነት ደቡብ አፍሪቃ ባይደርስና የሩቅ ምስራቅ የንግድ ግንኙነት ባይሆን ኖሮ ከላይ የተዘረዘሩት ታሪክዌ ሂደት አይከናወ ኑም ነበር? ሊላ ጥሩ ምሳሊ፤ አውሮፓዉያን ንግዳቸው ሰው በግልበቱ ያመረተዉን ምርት ብቻ ቢሆንና የሰው ልጅ በሰዉነቱ የተከበረ ቢሆን ዉጢቱ ምን ይመስል ነበር? ይህንን አንባቢ ተመራምረሕ ድረስበት ማለት አይቻልም፤ስለዚህ እዚህ ላይ ትንሽ ቆይታ አድርገን መወያየቱ አስፈላጊ ነው። በዚህ ሁለተኛው ታሪካዌ ሂደት ላይ የምንመለከተው ፖርቱጌስ በማወቅም ሆነ ባለማውቅ አሁን ለአለንበት ችግር ትልቁን መስተዋጽኦ አድርጓል በማለት እንወያያለን፤ በአፍሪቃ ዉስጥ የፖርቱጌስ ቅኝ ግዛቶች ስድስት ናቸው፤ አንጎላ፤ኬፕ ቨርድ፤ጊኒ ቢሳው፤ሞዛምቢክ፤ሳዎ ቶም፤ኢኳቶሪያል ጊኒ ናቸው፤ እነዚህ ተጠቃለው ሉሶፎን ይባላሉ ቋንቋቸዉ ፖርቱጊስ ስለሆነ። እነዚህን አገሮች በቅኝ ግዛት አስተዳድረው እነሱ የደሩሰብትን ስልጣኒ ለአፍሪቃዉያን ቢያክፍሉ መልካም ነበር፤ ነገር ግን የሰዉን ልጅ መሽጥና መለወጥ ስለጀመሩ ለሰው ልጅ ያተረፈው ዘላለማዌ እሮሮ ነው። ከታሪኩ ቀንጨብ አድርገን ብንመለከተው ይህንን ይመስላል፤ የአስራምስተኛው መቶ ዘመን ሲገባደድ ፖርቱጌስ የአፍሪቃን አህጉር ዙራዌን ዞረው በመጨረሽ ንግዱን ሙሉ በመሉ በቁጥጥራቸው ስር አድርገዉት ነበር፤ ከቅኝ ግዛታቻው የሚያገኙት ጥሬ ሃብት አልበቃ ብሎአቸው ጊኒ አካባቢ በምትገኝው ሳኦ በምትባል ደሲት ላይ የሱካር ማምረቻ ሁዳድ በመስራት ከአካባቢው አፍሪቃውያንን በጠመንጃና በዉስኪ በመለወጥ የነፃ አግልግሎት የሚስጥ ኃይል ከአዘጋጁ በኋላ ወደ አውሮፓ የሚላክ ስኳር ማምረት ጀመሩ፤ይህ የስኳር ምርት በጣም ተፈላጌ እየሆነ ስለመጣ ታላቅ የእስር ቤት በመገንባት ለሽያጭ የሚቀርቡትን አፍሪቃዉያንን ማከማቻ በማደረግ የሰው ልጅ እንደቃ መሽጥና መለወጥ ተጀምሮ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ አፍሪቃዉያን ለባርነት ተሽጠዋል፤ ዋልተር ሮድኒ የሚባሉ ጸሐፊ “አውሮፓ እንዲት አፍሪቃን ወደ ኋላ እንዳስቀሯት” በሚል መጽሐፋቸው ላይ እንደጻፉት ቢያንስ ከመቶ ሚሊዮን በላይ አፍሪቃዉያን ከአጠቃላይ አፍሪቃ አገሮች ለባርነት መሽጣቸዉን ከበቂ መረጃ ጋር አቅርበዋል፤ ነገር ግን የአውሮፓ ምሁራን ቁጥሩን እጅግ በማሳነስ ከ 9 እስክ 11 ሚሊዮን ሊደርስ ይችላል በማለት በታሪክ ማህደር ዉስጥ አስቀምጠዋል፤ ይህም ሆነ ያ የሰው ልጅ እንደክብት በሐራጅ የተሽጠበት ዘመን መሆኑን ሊካድ አይችልም። በዚህም ንግድ ተጠቃሚ የነብሩ አገሮች አሚሪካ፤ብራዚል፤ በአጠቃላይ የካሪቢያን ደሲቶች የስኳርና የጥጥ አምራች በመሆን ይታወቃሉ፤ ለአውሮፓ ኢንዱስትሪ መዳበርና ለቲክኖሎጂ ማደግ ትልቁን መስተዋጽኦ ያደረገ ከአፍሪቃ የመጣ የነፃ ጉልበት መሆኑን ታሪክ ሳይዘግበው መቅረቱ እጅግ በጣም አስዛኝ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ አውሮፓ አፍሪቃን እንደቅርጫ እንዲት እንደ ከፋፈሏት  በክፍል ሁለት እንመለከታለን።

No comments:

Post a Comment