።
✔በዚህ መዝገብ ወጣት ኡመር ሃሰን ከሌሎች ወጣቶች ጋር የቂሊጦ ማረሚያ ቤት ያቃጠልነው እኛ ነን ብላቹህ እመኑ በማለት ተደብድበው ሌላ ክስ እንደተመሰረበት ይታወቃል
።
✔ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት የመጡት መከላከያ ምስክሮች የድምፅ ቅጂ ስለጠፋ እና የ14ኛ ተከሳሽ መከላከያ ምስክር ስለጠፋ ውሳኔውን አልጨረስነውም በማለት ለታህሳስ 27 ለመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ተቀጠሩ
።
ቢቢኤን ታህሳስ 5/2008
።
በነ አህመድ እንድሪስ የክስ መዝገብ የተካተቱት 13 የደሴ ንፁሃን ወጣቶች በፀረ ሽብር ህጉ 652/2001 አንቀጵ 6/2 በመጥቀስ ሃይማኖታዊ መንግስት ልትመሰረቱ ነበር፣2004 አየ አከባቢው ሲካሄድ የነበረውን የአንድነት እና የሰደቃ ፕሮግራሞችን ተሳትፋቹሃል፣መንግስት በእስልምና ሃይማኖት ጣልቃ ገብቱዋል ብላቹሃል እንዲሁም መንግስት ደህንነቶች በጥይት የገደሏቸውን ሼህ ኑር ይማምን ገድላቹሃል በማለት በሃሰት መክሰሱ የሚታወቅ ሲሆን አቃቢ ህጉ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮች በማስደመጥ በደህንነት ሚመራው ፍርድ ቤት በወቅቱ የአቃቢ ህግ መሰረተ ቢስ ክስ እና ማስረጃዎች በመቀበል ተከላከሉ ሚል ብይን ከሰጠ ቡሃላ ንፁሃን ወጣቶችም በቅርቡ ከእስር የተፈቱትን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣የአዳማው ወጣት አብዱአዚዝ ጀማል እንዲሁም በእስር ሚገኙትን የታሪካችን ተራኪ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና የኮሚቴው ፀሃፊ አህመድ ሙስጠፋ ጨምሮ 90 የሃል የመከላከያ ምስክሮችን እና ማስረጃዎችን በማቅረብ ንፅህናቸውን በማቅረብ የተከላከሉ ሲሆን ጉዳያቸው ለ3 አመታት ያክል እየተመላለሱ ይገኛሉ እንደሚታወቀው ከነዚሁ ወጣቶች ጋር ለተከሳሾች የገንዘብ ድጋፍ አድርገሃል ተብሎ በሃሰት ተከሶ በጥር 5/2008 በመርዝ መርፌ በማረሚያ ቤት የተገደለው 9ኛ ተከሳሽ የነበረው ሙባረክ ይመር ይገኝበት የነበረ ሲሆን በወቅቱ የሙባረክ ክስ ተቋርጦ በአሁን ሰአት 13 ያክል ንፁሃን ተከሳሾች ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ እንደዚሁም በዚህ መዝገብ ወጣት ኡመር ሁሴን እና ሌሎች ወጣቶች የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ያቀጠልነው እኛ ነን ብላቹህ እመኑ በማለት በቶርቸር ካሰቃዩዋቸው ቡሃላ ከሌሎች ወጣቶች ጋር ክስ መመስረቱ ይታወቃል በዛሬው ዕለት ችሎት የቀረቡት ወጣቶች ፍርድ ቤቱ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት መተው ምስክርነት የሰጡት ምሰክሮች የድምፅ ፋይል ስለጠፋ እና የ14ተኛ ተከሳሽ መከላከያ ስለጠፋ መዘረገቡን መርምረን አልጨረስንም በማለት ፍትህ ተፈልጎ ለታህሳስ 27 ለመጨረሻ ፍርድ ውሳኔ ቀጠሮ ሰጥቱዋል በዛሬው ችሎት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ሌላ ክስ የተመሰረተበት ተከሳሽ ኡመር ሀሴን በሸዋሩ ቢት የደረሰበትን ስቃይ ለካንጋሮ ፍርድ ቤት አቤቱታ ሊያቀርብ ሲሞክር ዳኛዎቹ እድል ነፍገውታል
።
በነ አህመድ እንድሪስ መዝገብ የተጠቀሱት ሙስሊሞች:–
1,አህመድ እንዲሪስ ገበየው
2,አንዋር ኡመር ሰኢድ
3,ሳሊህ መሃመድ አብዱ
4,ሼህ አደም አራጋው አህመ
5,አብዱረህማን እሸቱ መሃመድ
6,ኢብራሂም ሙሄ ኢማም
7,ኡመር ሁሴን አህመድ
8,ይመር ሁሴን ሞላ
9,ሙባረክ ይመር(ረሂመሁላህ በማረሚያ ቤት የተገደለው ጀግና)
10,እስማኤል ሃሰን ይመር
11,ከማል ሁሴን አህመድ
12,አብዱ ሃሰን መሃመድ
13,አህመድ ጀማል ሰኢድ
14,መሃመድ ዩሱፍ መሃመድ ናቸው
በዛሬው ዕለት ቁጥሩ ከፍተኛ ህዝበ ሙስሊም እና ታላላቅ ኡለማዎች በፍርድ ቤት በመገኘት አጋርነታችንን ማሳየታቸው ታውቁዋል
No comments:
Post a Comment