Tuesday, November 17, 2015

የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የቅርብ ቤተሰብ በበርካታ ዜጎች ላይ የፈጸሙት ማጭበርበር ተጋለጠ


ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤት አባት የሆኑት አቶ አሰፋ ሩዎ ሂወራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ነዋሪዎችን የቤት ካርታ በመቀበል በአመት ከ25 ሺ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚከፍሉ አስታውቀው የባንክ ብድር ከወሰዱ በሁዋላ፣ ብድሩን ለመመለስ ሳይችሉ በመቅረታቸው የቤታቸውን ካርታ ያስያዙ ሰዎች ቤታቸው በሃራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ሚኒስትሩን ከለላ በማድረግ አቶ አሰፋ ራሳቸውን ኢንቨስተር ነኝ በማለት ከ18 ያላነሱ ግለሰቦችን ቤት ካርታዎች በማስያስ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከወጋገን ከባንክ ወስደዋል። ካርታቸውን የሰጡ ሰዎች በየአመቱ ይከፈላችሁዋል የተባሉትን ገንዘብ አላገኙም።
ወ/ሮ ምህረት ሆዬ ሮሶ፣ 300 ካሬ ሜትር የሚያወጣ ወይም 514 ሺ 945 ብር፣ አቶ ንዋይ ላቺቦ ኢርቤቶ 200 ካሬ ሜትር 400 ሺ 307 ብር፣ አቶ ንጉሴ ገብረ ፍቅር 200 ካሜ ቦታ ብር 383 ሺ 400 ብር፣ አቶ መሳይ መኮንን ተክሉ 150 ካሜ 364 ሺ 635 ብር፣ ገበየሁ ጋብሶ ጣለላ 180 ካሜ 318 ሺ 900 ብር፣ ጥሩነሽ ብርሃኑ ሃንኬሞ 200 ካሬ ሜትር 302 ሺ ፣ 100 ብር የሚያወጣ ንብረታቸው አደጋ የወደቀበት ሲሆን፣ በተመሳሳይ መንገድ የተጭበረበሩት መምህር ሽፈራው ቤታቸው ተወርሶ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል። የማጭበርበር ወንጀል የፈጸሙት ግለሰብ ክስ ይመስረትባቸው አይመስረትባቸው የታወቀ ነገር የለም።
Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment