ጷግሜን ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምስራቅ ሸዋ ዞን ናዝሬትና ሻሸመኔ ዙሪያ አሳሳ፣ ዶዶላ፣ አርሲ ነገሌ፣ አጄ፣ ኮፈሌ፣ ሄረሮ እና አዳባ በሚገኙ ሰባት ከተሞች የሚኖሩ ሙስሊሞች በግድግዳዎች ላይ የተቃውሞ ጽሁፎችን በመጻፍና በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ከድምጻችን ይሰማ ጋር አብረው እንደሚታገሉ አሳውቀዋል።
የሕዝበ ሙስሉሙ ተቃውሞ በአካባቢው ባለስልጣናት ላይ መደናገጥ የፈጥረባቸው መሆኑን አንዳንድ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ድምጻችን ይሰማ ትግሉን ወደ አንድ ደረጃ ለማሸጋገር እየሰራ መሆኑን ቀደም ብሎ አስታውቋል። የሳንቲም መሰብሰቡ ተቃውሞ እስካሁን ድረስ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ሌሎች የተቃውሞ መንገዶችም እንደሚገለጹ ይጠበቃል።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment