ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ የትግል ስትራቴጂውን በአዲስ መንገድ እንደሚቀይስ ማስታወቁን ተከትሎ፣ የመጀመሪያውን ትግል አንድ ቁጥር በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ በቅርቡ ፍርድ ቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ የሰጠውን ፍርድ ” የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ አምባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም” የሚል መፈክር በማሰማት ተቃውሞ አሰምቷል።
አሃዱን አሃድ፣ ትግላችን ይቀጥላል፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ ሳይፈቱ ሰላም የለም የሚሉ መፈክሮችም ተሰምተዋል። ገዢው ፓርቲ ሃይል በመጠቀም የሙስሊሙን ተቃውሞ ማፈኑን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ ሙስሊም ቀን ጠብቆ ያሰማው ተቃውሞ፣ ሙስሊሙ በሚደርስበት ጫና አንገቱን የደፋ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው።
ድምጻችን ይሰማ የተለያዩ የትግል ስትራቴጂዎችን በመንደፍ የሙስሊሙ ጥያቄዎች እንዲከበሩ አስፈላጊውን ትግል እንድሚያደርግ አስታውቋል።
Source:: Ethsat
No comments:
Post a Comment