Friday, August 14, 2015

በመጪው አመት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላል ተባለ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለም ላይ የሚታየውን የአየር መዛባት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግስታት እየገለጹ ነው። በምግብ እጥረቱ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትና ሌሎች ድሃ አገሮች ክፉኛ ሊጎዱ ይችላል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረው የምግብ እጥረት በባሰ ሁኔታ በያዝነውና በመጪው አመት ሊከሰት እንደሚችል ያስጠነቀቁት መንግስታቱ፣ የምግብ እጥረቱ ግጭቶችን ሊያባብስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
Source :http://ethsat.com/amharic/%e1%89%a0%e1%88%98%e1%8c%aa%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%88%98%e1%89%b5-%e1%8a%a8%e1%8d%8d%e1%89%b0%e1%8a%9b-%e1%8b%a8%e1%88%9d%e1%8c%8d%e1%89%a5-%e1%8a%a5%e1%8c%a5%e1%88%a8%e1%89%b5-%e1%88%8a%e1%8a%a8/

No comments:

Post a Comment