Tuesday, August 11, 2015

በኢትዮጵያ ወታደሮች ለተገድሉት አምስት ንፁሃን ሰላማዊ የሶማሊያ ዜጎች የአፍሪካ ህብረት ጦር ይቅርታ ጠየቀ

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት በሂራን ክልል ቡሎ ቡርዴ እና በለድ ወይኔ ከተማ ውስጥ ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሽማግሌዎቹ፣ ከአምስት በላይ ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎች በኢትዮጵያ ወታደሮች በግፍ መገደላቸውን ተናግረዋል። የሶማሊያ ምክትል የመከላከያ አዛዥ መሀመድ አደን ግድያው መፈፀሙን አምነው የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ይቅርታ ጠይቀውናል ብለዋል። ከዚህ ክስተት አንድ ሳምንት በኋላም የህብረቱ ወታደሮች ያልታጠቁ ንፁሃን ዜጎችን በደቡባዊ ሶማሊያ በማርካና ሁድሩ ከተሞች መግደላቸውን ሸበሌ ኒውስ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment