Wednesday, August 19, 2015

ከምርጫው ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውን ከ80 በላይ የፓርቲ አመራሮች መታሰራቸውን ሰመጉ አስታወቀ

ከምርጫው ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውን ከ80 በላይ የፓርቲ አመራሮች መታሰራቸውን ሰመጉ አስታወቀ
ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉ ባወጣው 137ኛ ልዩ መግለጫ፣ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውንና 83 የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መታሰራቸውን በስም ዘርዝሮ አቅርቧል።
በደብረማርቆስ ከተማ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም የተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ፣ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የተገደለ መሆኑን የቅርብ ቤተሰቦቹ ለሰመጉ መግለጻቸውን ጠቅሷል። በሚዳቀኝ ወረዳ አቶ ጊዲሳ ጨመዳ፣ በቆራ ወረዳ አቶ ገቢ ጥቤ፣ በማይካድራ ከተማ አቶ ታደሰ አብርሃ፣ በሶሮ ወረዳ አቶ ብርሃኑ አሪቦ እንዲሁም በግንቦ ወረዳ አቶ አስራት ሃይሌ ከፖለቲካ አመለካከታቸው ጋር በተያያዘ መገደላቸውን ገልጿል።
በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩ 83 ሰዎች በአንዳንዶቹ ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው መሆኑን የጠቀሰው ሰመጉ፣ አሀዙ ከዚህ በላይ ሊሆን ይችላል ብሎአል።
በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንደቀጠለ መሆኑን የገለጸው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ፣ አገሪቱ እጅግ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ሲል አክሏል።
በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ለሟች ቤተሰቦችም አስፈላጊውን ካሳ እንዲከፈላቸው፣ መንግስትም ጥቃቱን እንዲያቆም ሰመጉ ጠይቋል።

Source :http://ethsat.com/amharic/%e1%8a%a8%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab%e1%8b%8d-%e1%8c%8b%e1%88%ad-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%8b%ab%e1%8b%ab%e1%8b%98-6-%e1%88%b0%e1%8b%8e%e1%89%bd-%e1%88%98%e1%8c%88%e1%8b%b0%e1%88%8b%e1%89%b8%e1%8b%8d/

No comments:

Post a Comment