Wednesday, July 1, 2015

በአርባምንጭ የፌደራል ፖሊሶች ሲከታተሉት የነበረ መኪና መስመር በመጣሱ 7 ሰዎች ሞቱ


ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 19 ቀን 2007 ዓም ከጧቱ 1 ሰአት ላይ መድሃኒአለም በሚባል አካባቢ ሁለት መኪኖች ኮንትሮባንድ እቃ ጭነዋል በሚል ምክንያት ሲከተሉዋቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በድንገት ተኩስ በመክፈታቸው አንደኛው መኪና መስመሩን ስቶ ከወጣ በሁዋላ በመገልበጡ 7 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል።
አብዛኞቹ ሟቾች በማግስቱ ለሚደረገው የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የምረቃ ስነስርአት ለመሳተፍ የመጡ ናቸው። ነዋሪዎች እንደሚሉት አንደኛው መኪና በተኩሱ መሃል ሲያመልጥ ሌላው ግን በድንገት መስመሩን ስቶ ተገልብጧል።
በጉዳዩ ዙሪያ ስለደረሰው አደጋ የከተማውን መስተዳድር ለማናጋር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment