Thursday, July 23, 2015

መርከቡ ኃይሌና አበበ ቁምላቸው ለሀምሌ 20 ተቀጠሩ


10463041_743307185794942_2217112901280737100_n
ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት እየሰራችሁ ነው፣ ኦባማ ሲመጣ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሳችሁ መሆኑን ደርሰንበታል በሚል የታሰሩት አቶ መርከቡ ኃይሌና አቶ አበበ ቁምላቸው ለሀምሌ 20/207 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ዛሬ ሀምሌ 16/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት በዝግ ችሎት የቀረበው አቶ መርከቡ ኃይሌ ለውሳኔ ለሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡
በተመሳሳይ በቄራ ፍርድ ቤት የቀረበው አቶ አበበ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበት ለሀምሌ 20 ተቀጥሯል፡፡ አቶ አበበ የጊዜ ቀጠሮ ሲሰጥበት ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው፡፡ አቶ አበበ ቁምላቸውን ደህንነቶች ‹‹ከሌሎች አባላቶች ጋር በመሰባሰብ ሁከት ለመፍጠር እየሰራችሁ ነው›› በሚል ምርመራ እንደሚያደርጉበትና ድብደባም እንደሚፈጽሙበት ገልጾአል፡፡
በተመሳሳይ ሀምሌ 11/2007 ዓ.ም ባልታወቀ ምክንያት የታሰረው የቀድሞ አንድነት አባል አቶ ፍቃዱ በቀለ ካሳንቺስ የሚገኘው 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ምድር ቤት ውስጥ ብቻውን ታስሮ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
Source:: Zehabesha

No comments:

Post a Comment