(ዘ-ሐበሻ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያ መምጣት ጠቅሞናል በሚሉና መሳቂያ አድርጎናል በሚሉ ሃሳቦች የኢሕ አዴግ አባላት ለሁለት መከፋፈላቸውን የዘ-ሐበሻ የውስጥ ምንጮች አስታወቁ::
እንደምንጮቻችን ገለጻ በኢሕ አዴግ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ዲሞክራሲና ሰብአብዊ መብት አያያዝ በከፍተኛ ሁኔታ መተቸታቸውና ኢሕ አዴግ 100% አሸንፍኩ የሚለውን ምርጫ መሳቂያ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው:: በተጨማሪም ኢሕአዴጎች ባራክ ኦባማ እንደ አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግን የመሳሰሉ መሳሪያ አንስተው ድርጅቱን ለመጣል የሚንቀሳቀሱትን ድርጅቶች አሸባሪዎች እንዲልላቸው ፈልገው የነበረ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ እነዚህን ድርጅቶች በአሸባሪነት አለመፈረጃቸው በኢህ አዴግ አባላት ዘንድ ከፍተኛ የፖለቲካ ክስረትን አስከትሏል::
የኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ተከትሎ በኢሕአዴግ የይስሙላ የ100% የአሸንፌያለሁ የምርጫ ውጤት የተሳለቁት ከሱዛን ራይስ ጨምሮ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ሲሆኑ እነዚህም ሚድያዎች የኦባማን ኢትዮጵያ መሄድ ተከትሎ በምርጫው ውጤት ከመሳለቃቸው በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ መዘገባቸው አንዳንድ የኢሕ አዴግ አባላት “የኦባማ መምጣት በውጭ ሚድያዎች አጋለጠን; ለተቃዋሚዎች ጥቂት ወንበር ብንሰጥ ኖሮ ከዚህ ውርደት እንተርፍ ነበር” በሚል አቋም መከፈላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
ሲኤን ኤን; ዘጋርዲያን; ዩኤስ ኤ ቱደይ; ያሁ ኒውስ; ሮይተርስ; ፎክስ; ኤ ኤፍ ፒ: ኤፒ; ኤቢሲ; ኤንቢሲ; ፖለቲኮ; ቢቢሲ; ኤንፒአር; ኤቢሲ; አልጀዚራን ጨምሮ በየዓለማቱ ያሉ ትላልቅ ሚድያዎች የሕወሓት/ኢሕ አዴግን የሰብ አዊ መብት አያያዝና መሳቂያውን ምርጫ የኦባማን ጉብኝት ተከትሎ እያነሱ በሰፊው ተችተውበታል:: በዚህም የኢሕ አዴግ አባላት ደስተኛ እንዳልሆኑ ተገልጿል::
Source:: Zehabesha
No comments:
Post a Comment