Monday, June 8, 2015

በቡሌ ሆራ የኒቨርስቲ ተቃውሞ አስነስታችሁዋል የተባሉ ተማሪዎች ታገዱ


ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ግጭት ከተፈጠረ በሁዋላ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ለግጭቱ መነሳት መንስኤ ሆነዋል፣ ጥቃትም ፈጽመዋል ያላቸውን ሁለት ተማሪዎች
ከትምህርት ገበታቸው አግዷል። ተማሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
አንደኛው ተማሪ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዚዳንት መኪና በድንጋይ ወረውሮ ሰብሯል የሚል ክስ ሲቀርብበት ሌላው ተማሪ ደግሞ ጩቤ ይዞ ተገኝቷል የሚል ክስ ቀርቦበታል። ከታገዱት ሁለት ተማሪዎች መካከል አንደኛው በዚህ አመት ተመራቂ ነበር።

No comments:

Post a Comment