ሰኔ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ የግል ባለንብረቶች ወደ አዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤቶች ታፔላ ለመቀየር በሄዱበት ወቅት ከተለመደው የታፔላ ማስቀየሪያ አገልግሎት ክፍያ ውጪ ባልተጠበቀ ሁኔታ የ1ሺ ብር ቦንድ ካልገዛችሁ የሚል ግዳጅ ተጥሎባቸዋል ።
“አሁንስ ወዴት እንሂድ? ለማን አቤት እንበል?” በማለት የታክሲ ባለንብረቶች ሲያማርሩ ተሰምተዋል። ታክሲዎች ለ3 ወራት ያክል በአንድ አካባቢ ካሰሩ በሁዋላ ታፔላቸው ተቀይሮ ሌላ አካባቢ እንዲሰሩ ይገደላሉ።ይህን ታፔላ ያልያዙ ታክሲዎች ስራ መስራት ባለመቻላቸው፣ ቦንዱን ለመግዛት እንደሚገደዱ የታክሲ ባለንብረቶች ይናገራሉ።

Source:http://ethsat.com
No comments:
Post a Comment