Tuesday, May 26, 2015

የአፍሪቃ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን መግለጫ

የአፍሪቃ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን መግለጫ
የታዛቢዉ ቡድን አባላት ተዘዋዉረዉ ካዩአቸዉ የምርጫ ጣቢያዎች ከ21 ከመቶ በሚልጡት የድምፅ መስጪያ ኮሮጆዎች ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ባዶ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ ቢጠይቁ እንዳልተፈቀደላቸዉ፤ ኮሮጆዎቹ የቅደም ተከተል መለያ ቁጥር እንዳልተሰጣቸዉ እና የሐገር ዉስጥ ታዛቢዎች ተሳትፎ እጅግ ደከማ እንደነበር ቡድኑ አስታዉቋል።

ባለፈዉ ዕሁድ ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን አጠቃላይ ምርጫ የታዘበዉ የአፍሪቃ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን ዛሬ የመጀመሪያ ዘገባዉን ይፋ አድርጓል።የታዛቢዉ ቡድን መሪ በንባብ ባሰሙት መግለጫ ቡድኑ የድምፅ አሰጣጡ ሒደት ሠላማዊ መሆኑን አረጋግጧል።ይሁንና የታዛቢዉ ቡድን አባላት ተዘዋዉረዉ ካዩአቸዉ የምርጫ ጣቢያዎች ከ21 ከመቶ በሚልጡት የድምፅ መስጪያ ኮሮጆዎች ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ባዶ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ ቢጠይቁ እንዳልተፈቀደላቸዉ፤ ኮሮጆዎቹ የቅደም ተከተል መለያ ቁጥር እንዳልተሰጣቸዉ እና የሐገር ዉስጥ ታዛቢዎች ተሳትፎ እጅግ ደከማ እንደነበር ቡድኑ አስታዉቋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ መግለጫዉን ተከታትሎት ነበር።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ

Source:http://www.dw.de/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%89%83-%E1%88%95%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%89%B3%E1%8B%9B%E1%89%A2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%A1%E1%8B%B5%E1%8A%95-%E1%88%98%E1%8C%8D%E1%88%88%E1%8C%AB/a-18477177

No comments:

Post a Comment