Showing posts with label Konso Protest. Show all posts
Showing posts with label Konso Protest. Show all posts

Saturday, September 24, 2016

የኮንሶ ቀውስ: “ጥያቄያችን በኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል” አቶ ገመቹ ገንፌ የኮንሶ ኮሚቴ አባል “ጥያቄው የህዝብ ሳይሆን የጥቂቶች ነው” – የክልሉ መንግስት




konso
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ታትሞ የወጣው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ
አለማየሁ አንበሴ
ከኮንሶ የዞንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት የበርካቶች ህይወት ጠፍቶና በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለው ዜጎች የተፈናቀሉሲሆን የኮንሶ ህዝብ ኮሚቴ፤ ጥያቄያችን ወደ ኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል ብለዋል፡፡
በአካባቢው እስከ ትናንት ድረስ ግጭቶች መቀጠላቸውንና የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የኮንሶ ኮሚቴ አባል አቶ ገመቹ ገንፌ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን በሰሞኑ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና አስክሬናቸው እስከ ትናንት ድረስ ለቤተሰብ እንዳልተሰጠ ተገናግረዋል።
የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ አይረዲን በበኩላቸው፤ ግጭቱን ያስነሱትና በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉት የኮሚቴው አባላት ናቸው ይላሉ፡፡
“የፀጥታ ኃይሉ ጥፋቱ ከደረሰ በኋላ ነው ህዝቡን ለመታደግ ወደ አካባቢው የገባው፤ በአሁን ወቅት ግን በኮንሶ ምንም ግጭት የለም፤ ሰላማዊ ነው”፤ ብለዋል ኃላፊዋ፡፡
የኮሚቴው አባል አቶ ገመቹ፤ ጥያቄያችን በፌደሬሽን ምክር ቤት ተቀባይነት ካላገኘ በሪፈረንደም ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመጠቃለል ጥያቄ እናቀርባለን ያሉ ሲሆን ወ/ሮ ሂክማን በበኩላቸው የዞንነት ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው ምላሽ ተሰጥቶቷል፤ ከህዝቡ ጋር በተደረጉ ውይይቶች አሁን ባለው የወረዳ አወቃቀር ለመቀጠል ህዝቡ ፍላጎት እንዳለው ታውቋል ብለዋል፡፡
የፌደሬሽን ም/ቤት፤ የቀረበው ጥያቄ የአስተዳደር ጉዳይ ስለሆነ ሊመለከተው እንደማይችል ጠቁሞ፤ ም/ቤቱ የሚመለከተው የማንነት ጥያቄን እንደሆነ አመልክቷል፡፡ የኮንሶ ጥያቄ የማንነት አለመሆኑን በመግለፅ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል መንግስትና የኮንሶ ኮሚቴ አባላት በበርካታ ጉዳዮች ላይ እየተወዛገቡ ይገኛሉ፡፡

Friday, September 2, 2016

Konso strikes, Bodi blocks roads in protest in Southern Ethiopia

By Engidu Woldie
ESAT News (September 2, 2016)

Government offices and businesses were shut down on Thursday in Konso, south Ethiopia following announcement by the regional council that the petition by the people of Konso for self-administration has been scrapped.

The people of Konso submitted a petition signed by 50,000 people to the regional council demanding self-administration in their affairs but the council on Thursday announced that their demand has been thrown out of the window.

Protesting the decision by the regional council, government and other service employees have not reported to work for several days. Their salaries were also frozen, it was learnt.

The people of Bodi and Mursi meanwhile blocked main roads protesting the transfer of their land to companies for sugar plantation. Cadres and cronies of the TPLF have seized vast areas of land for investment in the south displacing the indigenous people.

Over 40 visitors to the plantation were unable to get out as the roads were blocked by the locals in protest.