Friday, October 2, 2015

የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ በጄኔቫ ውይይት ተካሄደ


መስከረም ፳ (ኅያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ውስጥ በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለወባ በሽታ የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አረጋገጡ
በዓመት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች በግድቦች አካባቢ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በወባ በሽታ የሚጠቁ ሲሆን በአዲሱ ዓመት ብቻ ከሰባ ስምንት በላይ አዳዲስ ግድቦች በመሰራታቸው ተጨማሪ ሃምሳ ስድስት ሽህ የወባ ተጠቂዎች እንደሚኖሩ ጥናቱ ጠቁሟል።
የውሃ ግድቦችን ለኃይል ማመንጫነት መጠቀም ከሰሃራ በታች ላሉት አገራት ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ከድህነት ለመውጣት ለሚያደርጉት ትግል አስተዋጽኦ ያለው ቢሆንም በግድቡ አካባቢ በቅርበት ለሚኖሩ ነዋሪዎች በወባና ውሃ ወለድ በሽታዎች ተጠቂ እንዳይሆኑ ታሳቢ የደረጉ ስራዎች አብረው መሰራት እንዳለባቸው ማላሪያ ጆርናል አክሎ ገልጿል።
ከሰሃራ በታች ባሉት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ካሉት አጠቃላይ አንድ ሽህ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ግድቦች ውስጥ ሰባት መቶ ሶስቱ በወባ በሽታ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ የተሰሩ ሲሆን በተለይ ከግድቦች አምስት ኪሎሜትር አቅራቢያ ያሉት አስራ አምስት ሚሊዮን ነዋሪዎች ውስጥ ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ለወባ የተጋለጡ ናቸው።በጋና አኮሶንቦ ግድብ፣በኬንያ ካምቡሩና በኢትዮጵያ ቆቃ ግድብ ዋነኞቹ የወባ ተጋላጭ ግድቦች መሆናቸውን ጥናቱ ጠቁሟል።

Source:: Ethsat

No comments:

Post a Comment