Friday, July 3, 2015

A high school teacher in Debre markos was found dead #Ethiopia‬ ‪#‎Debremarkos‬ ‪#‎RIP‬ ‪#‎Amhara‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

የሳሙኤል አወቀ አርባው ሳይወጣ ሌላ ወጣት መምህር ደብረ ማርቆስ ውስጥ ሞቶ ተገኘ።

- የአስክሬን ምርመራው ውጤት ግን መምህሩ ታፍኖ ወይም ታንቆ እንደተገደለ አመላካች ሆኗል።
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪ የሆነው ወጣት መምህር ምህረት ገበየሁ ደብረ ማርቆስ ውስጥ ሞቶ ተገኘ። መምህር ምህረት በአቸፈር ወረዳ (በአሁኑ ሰሜን አቸፈር) ይስማላ ጊዮርጊስ ከተማ በሚገኘው የሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት አስተማሪ የነበረ ሲሆን በዚህ ክረምት መግቢያ ወደ ደብረ ማርቆስ ያመራው accelarated medcine ለማጥናት እንደነበረ ታውቋል።
የሞቱ ፍንጭ እስካሁን ያልተረጋገጠ ቢሆንም የአስክሬን ምርመራው ውጤት ግን መምህሩ ታፍኖ ወይም ታንቆ እንደተገደለ አመላካች ሆኗል። በሰውነቱ ላይ ምንም አይነት ቁስል አለመገኘቱ ይህንን ጥርጣሬ ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪም ልብሱ ላይ የተገኙት የጭቃ ቅሬቶች ወጣቱ ከመሞቱ በፊት ከሰው ጋር ሲታገል እንደነበር የሚያመላክት ፍንጭ ሆኗል! ይህን ፍንጭ ወጣቱ አስተማሪ መምህር ምህረት በሰው ስለመገደሉ ማስረጃ ሊሆን ችሏል።
የወንድማችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን

Source : https://m.facebook.com/mereja.media/posts/999103546789152

No comments:

Post a Comment