Saturday, February 28, 2015

ከሃረር እስከ ጎዴ እንዲሁም ሃርጌሳ አፈሳው እና አፈናው ተጥውጡፏል

ምንሊክ ሳልሳዊ) ባለፉት ቀናቶች ውስጥ ወያኔ እና የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች ያደረጉትን ጦርነት ተከትሎ ከግድያው በተጨማሪ ከሃረር እስከ ጎዴ ያካልለ የመንገድ ላይ አፈሳ እና የቤት ለቤት አፈና እየተካሄደ እንደሆነ ከሰራዊቱ እስጥ የሚገኙት ወታደራዊ ደህንነቶች ተናግረዋል:: በልዩ ሃይል መሪነት እና በሕወሓት ጦር ተባባሪነት እየተፈጸመ ያለው አፈሳ እና አፈና የወያኔ ጦር ባልውፉት ቀናት የደረሰበትን ሽንፈት እና ኪሳራ ለማካካስ የጀመረው ሲሆን እስካሁን የቤት እመቤቶችን ጨምሮ ከ400 ሰዎች በላይ ተይዘው መታሰራቸው ሲነገር ዋና ዋና ናቸው የተባሉ የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች አባላት ወደ መሃል አገር መላካቸው ታውቋል::በዚህም መሰረት የስለላ ስራ ያካሂዳሉ የተባሉት አጋስ መሃመድ አብደላ እና አብዱላዚዝ አብዶ ቀሽር የተባሉ የአማጺ አባላት ይገኙበታል::አፈሳው እና አፈናው በሃረር በጎዴ በቀብሪበያህ በቀብሪ ደሃር በጅጅጋ በሃርሸክ እና በሰሜን ሱማሊያ ሃርጌሳ እየተካሄደ እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል:: በአንድ በኩል እንደራደር እያለ በአንድ በኩል በውጊያ የሚጠዛጠዘው ሰው በላው ወያኔ ምን ያህል የፖለቲካ ኪሳራ እና መበስበስ እንደሚጠቁም እና የኦጋዴንን ነዋሪዎች እያፈነ እና እያሰቃየ በየትኛው የሞላር ሚዛን ድርድር ላይ እንደሚቀመጥ እና ከነማንስ ነው የሚደራደረው የሚለው ጉዳይ ጥያቄ አስነስቷል:: ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦጋዴን አማጺ ሃይሎች እና በወየኔ ጦር መካከል በኦጋዴን ደገሃቡር አከባቢ ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ሲታወቅ በሰጋጋ አከባቢ የኦጋዴን አማጺ ሃይሎች ኮማንደር ተገለዋል:: የአማጺ ሃይሎች ተዋጊዎች በአከባቢው ከሚገኘው ልዩ ሃይል ተብሎ ከሚጠራው እና በወያኔ ጦር ጋር የአከባቢው ነዋሪዎች መታፈናቸውን ተከትሎ ከሃረር ከተማ 160 ኪሎሜትር ደቡብ ምስራቅ በምትገኝ በአኪርሚሽ ላስጋሎል በተባለ ቦታ መዋጋታቸውም ይታወሳል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39373#sthash.DADORkhB.dpuf


Source: zehabesha

No comments:

Post a Comment